የሁለቱ ሲኖዶሶች እርቅ መፍጠር ለሃገሪቱ ሰላም መሰረት የሚጥል ነው- ጠ/ሚ/ር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

የሁለቱ ሲኖዶሶች እርቅ መፍጠር ለሃገሪቱ ሰላም መሰረት የሚጥል ነው- ጠ/ሚ/ር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን አባቶች እርቅ በመፈፀማቸው መደሰታቸውን ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ገለፁ።

በዋሽንግተን ዲሲ በእርቁ ማብሰሪያ ጉባኤ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚንስትሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን አንድ እንድትሆን የምንፈልገው ሀገር ስለሆነች ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሂዶ ቤተ ክርስቲያን ለሁለም ሀገር የምትበቃና በሰላም፤ በአንድነት እና ልማት ረገድ ምሳሌ የምትሆንናት ብለዋል፡፡

ይህች ረጅም ጊዜ ያስቆጠረች ባለታሪክ ቤተክርስትያን ባለፉት አመታት አንድነቷ በለመጠበቁ ገናነታችንን አጥተናል፡፡

ሁለቱም ሊቃነ ጳጳሳት ለዚህ እርቅ መሳካት ላደረጉት ጥረት በእኔና በኢትዮጵያ መንግስት ምስጋናዬን አቀርባለሁ ብለዋል፡፡

አባቶች እንደ ልማዳቸውና ባህላቸው ሀገራችን ሰላም የሰፈነባት እንድትሆን በጸሎት እንዲያግዙም ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጠይቀዋል፡፡