ሃረር መንግስት በአፋጣኝ እርምጃ ካልወሰደ ከፍተኛ ግጭት ሊነሳ ይችላል።

ሃረር መንግስት በአፋጣኝ እርምጃ ካልወሰደ ከፍተኛ ግጭት ሊነሳ ይችላል። በሃረር ስርዓት አልበኝነት እየተስፋፋ በመምጣቱ ህዝቡ ምሬቱን እየገለጸ ነው :: በአካባቢው የሚታዬው ስርዓት አልበኝነት ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ በመምጣቱ መንግስት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።

በቄሮ ስም የሚነግዱ ወጣቶች ውሃ ወደ ሃረር ከተማ እንዳይገባ ለማድረግ የየረርን ትልቁን የውሃ ቧንቧ በመስበር ውሃ መከልከላቸው ታውቋል። በሃሮማያ አካባቢ ደግሞ ውሃ በቦቴ ወደ ሃረር እንዳይገባ ለማድረግ የመኪኖችን ቁልፍ ከሹፌሮች እየተቀበሉ በመከልከል ላይ ናቸው።

የክልሉ የውሃ ልማት ቢሮ ሃላፊ የሃይማኖት መሪዎችንና ታዋቂ ሰዎችን ሰብስበው በቄሮ ስም የሚነግዱትን ወጣቶች እንዲለምኑዋቸው ጠይቀዋል። የሃረር ህዝብ በውሃ ጥም እየተጎዳ በመሆኑ መንግስት በአፋጣኝ እርምጃ ካልወሰደ ከፍተኛ ግጭት ሊነሳ ይችላል።

በአባድር ወረዳ ዜሮ አምስት ቀበሌ አካባቢ ደግሞ የቄሮ አባላት ነን የሚሉ “ቤት ልቀቁ” እያሉ በማስፈራራት ላይ ሲሆኑ፣ ቤት እንዲለቁ የሚገደዱት ደግሞ የሌሎች ብሄር ተወላጆች ናቸው።

( ኢሳት ዜና ሃምሌ 18 ቀን 2010 ዓ/ም )