በአማራ ክልል ከ30 ሺህ ሄክታር በላይ የሰብል ምርት በአንበጣ መንጋ ጉዳት ደርሶበታል


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋሁን መንግሥቴ የአንበጣ መንጋው በክልሉ 4 ዞኖች፣ 18 ወረዳዎች በ136 ቀበሌዎች መከሰቱን ለቢቢሲ ተናግረዋል። የአንበጣ መንጋው 87 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ በሰብልና በእንስሳት መኖ ላይ ጉዳት አድርሷል የሚሉት አቶ ተስፋሁን፣ ከእነዚህም መካከል 30 ሺህ 500 ሄክታር የሚሆነው የሰብል ምርት መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።…