በመተከል ዞን በንጹሃን ላይ የሚፈጸመው ጥቃት የፖለቲካ ፓርቲዎች እጅ አለበት ተባለ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በመተከል ዞን በንጹሃን ላይ የሚፈጸመው ጥቃት በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ፖለቲካ ፓርቲዎች እጅ አለበት… የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን
(ኢዜአ) በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በንጹሃን ላይ የሚፈጸም ጥቃት የፖለቲካ ፓርቲዎች እጅ እንዳለበት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
በጥቃቱ የተጠረጠሩ ከ500 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና አካባቢውን ወደነበረበት ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለመመለስ በኮማንድ ፖስቱ እየተሰራ መሆኑንም ገልጿል።
የኮሚሽኑ ወንጀል ምርመራ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ኮማንደር አምሳሉ ኢረና ለኢዜአ እንዳሉት አገራዊ ለውጡን ተከትሎ ከ2010 እና 2011 ዓ.ም በካማሺና አሶሳ ዞኖች የጸጥታ ችግሮች ቢከሰቱም በሂደት መፈታታቸውን አስታውሰዋል።
ነገር ግን በመተከል ዞን የሚያጋጥሙ የጸጥታ ችግሮች አሁንም መቀመጠላቸውን ገልጸው፤ ችግሮችን ለማስቆም ሃላፊነታቸውን በአግባቡ ያልተወጡ አመራሮችና የጸጥታ አካላትን ተጠያቂ ለማድረግ ሲሰራ እንደነበር ተናግረዋል።
ክልሉ የተለያየ ማንነት ያላቸው ዜጎች በአብሮነት ተሳስበው የሚኖሩበት እንደነበረ ገልጸው፤ በቀጣይም የዜጎች በሰላም አብሮ የመኖር እሴት ተጠብቆ እንዲቀጥል ግጭት ቀስቃሽ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በዞኑ ከሰሞኑ የተከሰተውን ጨምሮ በተደጋጋሚ በንጹሃን ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች በህዝብ ስም የተቋቋመው የጉምዝ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ጉህዴን/ የተሰኘ ድርጅት እና ሌሎች ፓርቲዎችም እጅ እንዳለበት ጠቅሰዋል።