በደሴ ሸዋበር መስኪድ ላይ ጥቃት ያደረሱ ሰወች በመሐል አገር በድብቅ ለሽብር የሰለጠኑ መሆናቸውን ተናገሩ።

የደሴ ሸዋ በር መስጂድ በአሁኑ ሰአት!!!

እውነታው እየጠራ ነው!!!!!!

የወሎ ምድር ከፋፋይነትን የሚሸከምበት ጫንቃ የለውም!!!!

በአሁኑ ሰዓት በደሴ ሸዋበር መስጅ ቅጥር ግቢ ህዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው።
የከተማው አስተዳደር የለተሰብሳቢው ንግግር ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
የማታው የሸዋበር ጥቃት ከተነገረው በላይ የገዘፈና በእጅጉ የሰፋ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል።
ሌሊቱን ሙሉ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከፀጥታ ሀይሎች ጋር በመሆን ጥቃት አድራሾችን ለመያዝ በተደረገው እንቅስቃሴ ከ59 በላይ ሰወች ተይዘዋል።
የተያዙት ጥቃት አድራሾች ከሌላ አካባቢ የመጡ መሆናቸውና አብዝሀኞቹም አማርኛ ቋንቋ እንደማይችሉ ነው የታወቀው።

የጥቃት አድራሾቹ የመጡበት ቦታ በፖሊስ ሲጣራ ከኩናማ ጎጃም ጎንደር ከትግራይ ከሱዳን ድንበር ከጋቤላ ከቤኒሻንጉል ና ከሌላም አካባቢ የመጡ መኖራቸውን ነው።
ከሰወቹ ጋር በተወሰነ መልኩ በአረበኛና በእንግሊዘኛ ለመግባባት ተሞክሯል።

እጅግ በሚያስገርምና በሚያስደንቅ ሁኔታ ህዝበ ሙስሊሙ በማያውቀው ሁኔታ ድብቅ የማሰልጠኛ ቦታ በመሀል ከተማ አዘገጅተው ሲያሰለጥኗቸው መቆየቱን የተያዙት ሰወች ለፖሊስ ገልፀዋል።

የነዚህ ጥቃት አድራሾች መሰባሰብ በዋናነት የቀን ጅቦች የወንጀል ሰንሰለት እንዳለበት ነው መረዳት የተቻለው።

በአሁኑ ሰዓት ከስሜታዊነት በፀዳ መልኩ ወይይት እየተካሄደ ነው ።

((የዘገባው ምንጭ የቢላል ልጆች የሰላም ዘቦች ነው))

በደሴ ሸዋበር መስጂድ ላይ በተከሰት የሽብር አደጋ ጉዳት ከደረሰባቸው ሰወች አንዱ


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE