ፓትርያርክ አቡነ መርቆሪዎስ ወደ ቀድሞ መንበራቸው እንዲመለሱ ሲኖዶሶቹ እንዲዋሀዱ ተወሰነ።

በሁለቱ ሲኖዶሶች መካከል በመካሄድ ላይ ያለው ድርድር ዓላማውን በማሳካት ብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ወደ ቀድሞው መንበራቸው እንዲመለሱ ውሳኔ እንዳስተላለፈ ተገልጾልናል።

ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውና በውጭ የሚገኘው ሲኖዶስ ከአሁን በኋላ አንድ ውህድ ሲኖዶስ ሆነው መቀላቀላቸው ተጠቁሟል።በስብሰባው ላይ የነበሩ በሙሉ በጋራ በአንድ ድምፅ ውሳኔውን በጭብጨባ ደግፈውታል ።

ይህ ታላቅ ዜና ከሁለት ሽህ ዓመታት በላይ ላስቆጠረችው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን አማኞችና በአጠቃላይም ለኢትዮጵያ ህዝብ እጅግ አስደሳች ዜና ነው። ይህ ስምምነት ሊገኝ የቻለው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ባደረጉት ጠንካራ ጥረትና ድጋፍና እንደሆነ የሚታወቅ ነው።

ዝርዝሩን እንደደረሰን እናቀርባለን ።