ሰራተኞች የኢትዮጵያ አየር መንገድን አማረሩ ።

መረጃ ዶት ኮም

በኢትዮጵያ አየር መንገድ በአገልግሎት ሰጪ ስራ ኤጀንሲዎች ስር ተቀጥረው የሚሰሩ ሰራተኞች አየር መንገዱን አማረሩ ።

በባርነት ተሽጠናል ፣ የዘር መድልዎ ይደረግብናል ፣ የስራ እድገት የለንም ፣ ደምወዛችንን በግማሽ ተነጥቀናል ሲሉ አቤቱታቸው ለዶክተር አብይ አሕመድ እንዲደርስና በአየር መንገዱ ላይ ለውጥ እንዲደረግ አጥብቀው ጠይቀዋል። በአየር መንገዱ ውስጥ እድገት ለማግኘት በስራ አገልግሎትና በትምሕርት ደረጃ ሳይሆን በዘር ቆጠራና በዘመድ አዝማድ ነው ብለዋል። ሰራተኞቹ ከፍተኛ በደልና ማመናጨቅ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ በስራችን ላይ ተፅእኖ ፈጥሯል ሲሉ ይናገራሉ።

አትላስ ፣ ግሎባል ፣ፋየር የጽዳት አገልግሎት ፣ አዲስ ጠቅላላ አገልግሎት ሰጪ ማህበር፣የተባበሩት አገልገሎት ሰጪ ማህበር ተብለው የሚጠሩና በአየር መንገዱ ውስጥ የስራ ኤጀንሲ እንደሆኑ የተነገረላቸው ድርጅቶች የ አየር መንገዱ አመራሮች በዘር ሰንሰለት ያቋቋሙት እና አየር መንገዱን በአገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ስም ለመመዝበር የሚሰሩ ሰራተኞችን ከእንሰሳ በታች በማየር በደል የሚያደርሱ መሆኑን ሰራተኞቹ ይናገራሉ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ከፍተኛ አቤቱታ የሚቀርብበት ሲሆን በተለይ በዘረፋና በዘረኝነት ስሙ በስፋት ይነሳል። እነዚሁ በአገልግሎት ሰጪ ስራ ኤጀንሲ ስር ተቀጥረው የሚሰሩ ሰራተኞችም በዚህ ይስማማሉ ። ዶክተር አብይ አሕመድ አቤቱታቸውን እንዲያዩላቸው አጥብቀው ጠይቀዋል። (ምንሊክ ሳልሳዊ)


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE