ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ በትግራይ ይካሄዳል፤ በትግራይ የተካሄደው ምርጫ ተቀባይነት የለውም- የተወካዮች ምክር ቤት

‹‹ምርጫው በትግራይ ክልልም ይካሄዳል›› – አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ

(ሪፖርተር ጋዜጣ)

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ የሆኑት አቶ ታገሰ ጫፎ በ2013 ዓ.ም. እንዲካሄድ የተወሰነው አገር አቀፍ ምርጫ በመላ አገሪቱ እንደሚካሄድ መግለፃቸውን ሪፖርተር አስነብቧል።

በአሁኑ ወቅት በመንግሥት እና በሕዝቦች መካከል ያለው ማኅበራዊ ውል ሕገ መንግሥቱ እንደሆነ የጠቀሱት አፈ ጉባዔው፣ በዚህም ምክንያት ሁሉም አካል ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥቱ ያቋቋማቸው ተቋማትን ማክበርና በሕግ መሠረት የሚወሰኑትን መቀበል ግዴታ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከነዚህ ተቋማት መካከል አንዱ ፌዴሬሽን ምክር ቤት መሆኑን የጠቀሱት አፈ ጉባዔው ምክር ቤቱ በትግራይ የተካሄደው ምርጫ ተቀባይነት እንደሌለው መግለጹን በመጥቀስ 6ኛው አገራዊ ምርጫ በትግራይም እንደሚካሄድ ተናግረዋል።