የራያ አላማጣ ነዋሪዎች ዶክተር አብይን ደግፋቹሀል የሚል ግልፅ ክስ ተመሠረተባቸው።


በራያ አላማጣ ወረዳ በዋጃ ከተማ ባለፈው ቅዳሜ በተደረገው ዶክተር አብይ የሚያካህዱትን አገር አቀፋዊ ፖለቲካዊ ለውጥን በመደገፍ የወጣውን ህዝብ አስተባብራችኋል ተብለው ሰኞ ሌሊት ታፍነው የተወሰዱት ወጣቶች
1) ሞላ ዝናቤ
2) ተረፈ አርብሴ
3) መምህር አማረ ደሳለኝ
4) ጥጋቡ ገ/ማሪያም
ዛሬ አላማጣ የገጠር ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ እንደሆኑ ተነግሮ ቤተሰብ አይቷቸዋል፡፡ ወደማያዉቁት አካባቢ ተወስደው እንደነበርና አካላዊ ድብደባ እንደደረሰባቸው ለማረጋገጥ ችያለሁ፡፡
ፖሊስ ያቀረበባቸው ክስ የሚከተለው ሆኖ ለ14 ተቀጥረዋል፡፡
1) ዘረኝነት ይጥፋ ብላችኋል
2) የዶ/ር አብይ ምስል ያለው ትሸርት ለብሳችኋል
3) ባለስልጣንን ሰድባችኋል
4) አርማ የሌለው ሰንደቅ አላማ ይዛችኋል
5) ቆቦና ወልድያ ሄዳችሁ ተሰብስባችኋል
6) ዶ/ር አብይ እያስመዘገበ ያለውን አገራዊ ለውጥ እንደግፋለን ብላችኋል
7) የተረጋገጠውን ማንነት ጥቂጦቹ ናቸው፡፡
ተጨማሪ ፖሊሶችና ፖለቲካኞች የተነገሯቸው ሃይለቃሎች
አሁንም የጠነከርንና የማንገፋ ሃይል ነን
ልትገዳደሩት ከማትችሉት አካል ጋር ለመጋፈጥ አትመክሩ የሚሉ ዘግናኝ የቅኝ ገዥ ሃይለቃሎች እንደነበሩ ተነግሮኛል፡፡

ህዝብን በማፈን ፤ በማሰቃየትና ፤ ህጋዊና ህገምንግስታዊ ጥያቄን ለመጨፍለቅ በመሞከር ጥያቄያችንን ወደፊት ከመግፋት ወደ ኋላ አንልም፡፡ ማንነታችንና ክብራችን ከትህነግ ልምስ መዳፍ የምንወስድበት ጊዜ ቅርብ ነው፡፡