የኤርትራው የብሄራዊ ውትድርና አገልግሎት አንሳተፍም ያሉ የታሰሩበት አዲ አበይቶ የተባለውን ወህኒ ቤት ተዘጋ

የኤርትራው የብሄራዊ ውትድርና አገልግሎት አንሳተፍም ያሉ የታሰሩበት አዲ አበይቶ የተባለውን ወህኒ ቤት ተዘጋ

ከሶስት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት በኋላ ወደ ሀገራቸው የተመለሱት የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በርካታ እስረኞችን የያዘው የብሄራዊ ውትድርና አገልግሎት አንሳተፍም ያሉ በርካታ ኤርትራውያን የታሰሩበት አዲ አበይቶ የተሰኘውን ማረሚያ ቤት መዝጋታቸው ተነግሯል።

እንደ ዘገባው ከሆነ በእስር ቤቱ ውስጥ የብሄራዊ ውትድርና አገልግሎት አንሳተፍም ያሉ በርካታ ኤርትራውያን የታሰሩበት መሆኑ ታውቋል።
በዛሬው እለት ወህኒ ቤቱ የተዘጋና እስረኞቹም ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተቀላቅለዋል። አዲ አበይቶ ማረሚያ ቤት ከዋና ከተማዋ አስመራ ፬ ኪሎ ሜትር ያህል ወጣ ብሎ የሚገኝ ነው።