በኦሮሚያ ክልል የተማሪዎች ምዝገባ መጓተት ያሳደረው ስጋት

በኦሮሚያ ክልል ከነሐሴ 20 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ሲደረግ በነበረው የተማሪዎች ምዝገባ ወደ ትምህርት ቤት ለመመለስ የተመዘገቡት ተማሪዎች 13 በመቶ ያህሉ ብቻ ናቸው። የክልሉ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቶላ በሪሶ ለዶይቼ ቬለ እንደገለጹት ተማሪዎች ወደ ቀጣዩ ክፍል በቀጥታ እንዲሸጋገሩ መወሰኑ ተማሪዎች እንዲመዘገቡ ያበረታታል።…