የሸገር ፓርክ ምረቃ ስነ ስርዓት ዛሬ እየተካሄደ ነው።

የሸገር ፓርክ ምረቃ ስነ ስርዓት ዛሬ እየተካሄደ ነው።
በስነ ስርዓቱ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶክተር) እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጨምሮ ሌሎችም ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የሀይማኖት አባቶች እና የኅብረተሰብ ተወካዮች እየታደሙ ነው፡፡
ለፓርኩ መገንባት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት በተለይም ለቻይና መንግስት እና ለሌሎች አካላት እውቅና ተሰጥቷል።
በቻይና መንግስት ድጋፍ የሚከናወነው እና የሸገር ማስዋብ ፕሮጀክት አካል የሆነው የወንዝ ዳርቻ አረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ግንባታ መስከረም 20 ቀን 2012 ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት መጀመሩ ይታወሳል፡፡
የወዳጅነት አደባባይ የሚል ስያሜ የተሰጠው ፓርኩ ከሸራተን ሆቴል ፊት ለፊት ያለው 42 ስኩዌር ኪሎ ሜትር መሬት ላይ ያረፈ ነው።
በፕሮጀክቱ የስብሰባ፣ የጥበብ ማቅረቢያ ስፍራ፣ የህፃናት መዝናኛ ማዕከል እና የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ማዕከላት ያካተተ ነው።