“የመደመር” የልቀት አስተሳሰብ ግቡን የሚያፋጥነው ባለስልጣናት ለሰሩት በደል ሕዝብን በይፋ ይቅርታ ሲጠይቁ ነው። (ይድነቃቸው ከበደ )

ዶ/ር አብይ እባክዎን!
.
እርስዎ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ እጅግ በጣም አበረታች የሆነ የለውጥ ሂደት በአገራችን እየታየ ነው። ለዚህም የአንበሳውን ድርሻ እርስዎ እና በእርስዎ ዙሪያ የሚገኙ የለውጥ ኅይሎች ትልቁን ድርሻ ይወስዳሉ።
.
ሆኖም ግን ! የመንግስት ሹመኞች ከዚህ ቀደም በሥልጣን ዘመናቸው በህዝብ እና በአገር ላይ ለፈጸሙት ወንጀል እና በደል መጠየቅ ሲገባቸው ፤ አንዱን በሹመት ሌላው በክብር እና በማዕረግ በመሸኘት ከሕዝብ ዐይን ለመሰወር የሚደረገው ጥረት የተጀመረው የለውጥ ጉዞ የሚደግፍ ሣይሆን በለወጡ ላይ መጥፎ ጥላ የሚያጠላበት ነው።
.
እነኚህ ተጠያቂ የመንግስት ባለሥልጣን በሥልጣን ዘመናቸው ሌላው ቢቀር ለሰሩት አስከፊ እና አሰቃቂ በደል በህግ መጠየቃቸው ቀርቶ ሙገሳና ሹመቱ ልጎም ሊበጅለት ይገባል ። ከዚህም ከፍ ሲል ለሰሩት በደል ሕዝብን ይቅርታ መጠየቅ ይገባቸዋል ! ይህ ሲሆን ነው “የመደመር” የልቀት አስተሳሰብ ግቡን የሚያፋጥነው ።
.
(ይድነቃቸው ከበደ )