የኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል በነፍስ ማጥፋትና በአስገድዶ መድፈር ከታሰሩ የህግ ታራሚዎች ውጭ ሁሉንም እስረኞችን ፈታሁ አለ።

የኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል በነፍስ ማጥፋትና በአስገድዶ መድፈር ከታሰሩ የህግ ታራሚዎች ውጭ ሁሉንም ታራሚዎች መፍታቱን አስታወቀ፡፡


የክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ እድሪስ እስማኤል እንደገለፁት ክልሉ በየጊዜው የህግ ታራሚዎችን ሲለቅ ቆይቶ አሁን ላይ በእስር ቤት የነበሩ 150 እስረኞችን ለቋል፡፡
ከእነዚህ ውስጥ 17 እስረኞች የኦጋዴን ነፃ አውጪ ግንባር ኦብነግ አባላት መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡
በእስር ላይ እንዲቀሩ የተደረጉት በአስገድዶ መድፈርና በነፍስ ማጥፋት የታሰሩ መሆናቸውን ለኢቢሲ በስልክ ገልፀዋል፡፡
ከዚህ በኋላ የእስረኞች ማቆያ የነበሩ እስር ቤቶችን ወደ እምነት ቦታነት ለመለወጥ ይሰራልም ብለዋል፡፡


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE