የአዲስ አበባ ፖሊስ የአብዲ ኢሌን ተቃዋሚዎች ስብሰባ በኃይል አስቆመ ፤ ጋዜጠኞችን አንገላታ።

አብዲ ኢሌ በሶማሌ ክልል ብቻ ሳይሆን አዲስ አበባ ላይም ያሻውን ማድረግ እንደሚችል በተግባር አሳይቷል

(የኋላሸት ዘሪሁን)

አብዲንና አገዛዙን እሚቃወሙ የክልሉ የሃገር ሽማግሌዎች የሶማሌ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ሶህዴፓ) አባላት ዲያስፖራዎችና ምሁራን በተገኙበት ዛሬ ሃምሌ 4/2010 ዓም ከጠኋቱ 3:30 ጀምሮ በፍሬንድ ሺፕ ኢንተርናሽናል ሆቴል ተደሬጎ የነበረውን ጋዜጣዊ መግለጫና የውይይት መድረክ በ አብዲ ደጋፊዎች አማካኝነት ሊቋረጥ ችሏል አንዳንዶች ላይም ድብደባ ደርሷል

የፀጥታ አካላት በቦታው ላይ ተገኝተው የነበረ ቢሆንም ወደ ሆቴሉ በመግባት ሁከት የፈጠሩትን ቡድኖች ማስቆም ተስኗቸዋል ይልቁንም የፀጥታ አካላቱ ችግር የፈጠሩትን ሰዎች ከመከልከል ይልቅ ጋዜጠኞችን ፎቶና ቪዲዬ ካላጠፋችሁ በማለት ሲያውኩ ና ሲያንገላቱ ነበር

የአብዲን ፎቶ ያለበት ቲቸርት የለበሱት እነዚሁ አካላት የ አዲስ አድማሷን ጋዜጠኛ ናፍቆት ዬሴፍምን ለመደብደብ ሲጋበዙና እጇን ይዘው ሲያዋክቧት የነበሩ ሲሆን የያዘችውን ስልክ ሊነጥቋት ሲታገሏት እንደነበረ ታዝቤያለሁ ሌሎችንም ካሜራቸውን ተነጥቀው ያነሱትን ፎቶና ቪዲዬ ሲጠፉባቸው የነበረ ሲሆን ይሄም እሚያሳየው አብዲ ሱማሌ ክልል ላይ ብቻ ሳይሆን አዲስ አበባም ጭምር ያሻውን ማድረግ እንደሚችል ነው

ቦሌ እሚገኘው ፍሬንድ ሺፕ ኢንተርናሽናል ሆቴል ከስብሰባ አዳራሹ የጀመረው አምባ ጓሮ በአጠቃላይ የሆቴሉን እንቅስቃሴ አውኮት የነበረ ሲሆን በዚህም ሳያበቃ መንገድ በመዝጋት በስብሰባው ላይ የነበሩትን ሰዎችን አናስወጣም በማለት በአካባቢው ላይ ለግማሽ ሰዓት ያህል የመኪናና የእግረኛ እንቅስቃሴ ተቋርጦ ነበር

በጣም እሚያስገርመው ደግሞ በቦታው ላይ የአዲስ አበባና የፌደራል ፖሊስ አባላት ቢኖሩም ምንም አለመፈየዳቸው ነው

ከትላንት ወዲያ በድብቅ ወደ አዲስ አበባ የገቡ ከ ኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል የመጡ የሃገር ሽማግሌዎችና የጎሳ መሪዎች “ስንመለስ እሚጠብቀን ሞት መሆኑን እያወቅን ነው መፍትሄ ፍልጋ የመጣነው ዶ/ር አብይ ና መንግስታቸው በአስቸኳይ መፍትሄ ካልሰጡን ሰውየው ከ እስር የተረፉ ልጆቻችንን ይጨርስብናል “ያሉ ሲሆን

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር የነበሩ አቶ አቡዱል ፈታህ በ በኩላቸው “ዛሬ ቦሌ ላይ እሚገኝ ሆቴል ውስጥ ገብተው የ ደበደቡን የአብዲ ሰዎች ከዚህ ስንወጣ አፍነው እንደማይወስዱን ምንም ዋስትና የለንም ” በማለት ስጋታቸውን ገልፀዋል።

በነገራች ላይ ለያዥ ለገናዥ ካስቸገሩ ተደባዳቢዎች መሃል የአብዲ ደጋፊ የሆኑ የፖርላማ አባላት በግንባር ቀደምነት ይገኙበታል


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE