የሀገሪቱ ክንፍ የሰበረው ጀኔራል ክንፈ ዳኘው!

ክንፈ ዳኘው የሜቴክ ሀላፊ እያለ በርካታ ፕሮጀክቶች ተጀመሩ ተባለ። ለምሳሌ ትራንስፎርመር። ሜቴክ ገበያ እንዲያገኝ ከውጭ የሚገቡ ትራንስፎርመሮች ተከለከሉ። መብራት ሀይል ከሜቴክና ከሜቴክ ብቻ እንዲገዛ ተደረገ። ተቋማትም ግዴታ ተላለፈባቸው!

የሜቴክ ትራንስፎርመሮች ገና ኃይል እንደነካቸው መጋየት ጀመሩ። ወይ ለጥገና ካልሆነም እንደ አዲስ የሚገዙት ከሜቴክ ነው። በተዘዋዋሪው የኢፈርት ንብረት የሆነው ሜቴክ በየ ቀኑ በጥገና እና በግዥ ይጨናነቃል። የሚቆጣጠረው ክንፈ ዳኘው!

ይህ የሜቴክ ፎርጅድ ያስመረራቸው ባለሙያዎች ግልፁን ተናገሩ። ነገር ግን ሜቴክ መስማት አይፈልገም።ጉዱ በስፋት እንዳይሰማበት ግን ባለሙያዎችን አሳሰራቸው።

የሜቴክ እቃዎች እርባና እንደሌላቸው እየታወቀ በርካቶች ዝምታን መረጡ። ላለመታሰር። ይገዛሉ ይበላሻል። ይጠገናል አይሰራም። “የመንግስት ንብረት ነው!” እየተባለ ብዙ ከሰረ። መብራት ጠፋ። ሀገር በጨለማ ተዋጠች። እነ ክንፈ ዳኘው ናቸው ይህን የሚያደርጉት!

አንድ የመብራት ኃይል ሀላፊነት ቦታ የሚሰራ ሰው አዝኖ ያጫወተኝ የዚህን ክንፈ የሚባል ሰው ጉዳይ ነው። ትራንስፎርመር ብቻ አይደለም። የመኪና ክፍሎችንም እሰራለሁ አለ። ግን አይሰራም። “አንዱ መኪና ጫንጮ፣ አንዱ አባይ፣ አንደኛው አዲስ አበባ ቆመ።” ይላል። ሶስቱም እነ ክንፈ የሰሯቸው ናቸው። መገጣጠሚያዎቹን! ሲያስጠግኗቸው ደግሞ መንገድ ላይ መኪና ሲንገጫገጭም ሊበላሽ ይችላል አለ። ይህ ያስመረረው አመራር በቀጥታ ለክንፈ ፃፈ። “መገጣጠሚያዎቹ አይረቡም” ብሎ። ክንፈ አበደ! “አምጡልኝ! ይታሰር!” አለ። ደግነቱ ሰውየው ቀድሞ ሰማ። ከሚሰራበት ባህርዳር ጠፋ!

በክንፈ ዳኛው የሚመራው ሜቴክ እሰራዋለሁ ያላለው ነገር አልነበረም። ግን የማይሰራ። አክስር! መብራት እንዳጠፋው ሁሉ ብዙ ነገር አጥፍቷል። ክንፈ የሀገር ክንፍ ሰብሯል!

ይህ ክንፈም በሰላም ተሰናበተ! ሳይጠየቅ!


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE