ደብረ ማርቆስ ላይ ፖሊስ በረከት ስምዖንን ከህዝቡ ለማሸሽ ተኩስ ከፍቷል።

አለመረጋጋቱ ቀጥሏል።ጥይት እና አስለቃሽ ጋዝ ወደ ህዝቡ እየተተኮሰ ነው። የመኪናዉ ሹፌር አምልጧል። አብሮት የነበረ አንድ ሌላ ሰው( ሁለት መታወቂያ ተይዞበታልን ) አሁን ፖሊስ ጣቢያ ይገኛል። ረብሻው ወደ ትልቅ ሰው እና ማርሲላስ ሆቴል ተስፋፍቷል። ማርቆስ ከበረከት ጋር የነበረው የማርቆስ ከንቲባ አማረ አለሙ ቤት በአሁን ሰዓት እየተቃጠለ ነው!

የበረከት መኪና ዉስጥ ብዙ ዶክመንቶች ፣ካሜራ፣ ላፕቶፕ ተይዘዋል። መኪናዉ ተሰባብራለች ። የበረከት ሰምዖን V8 መኪና በደብረ ማርቆስ እንዲህ በእሳት ጋይቷል።

ደብረ ማርቆስ ላይ ፖሊስ በረከት ስምዖንን ከህዝቡ ለማሸሽ ተኩስ ከፍቷል። እንዲሁም ከብርሸለቆ የተነሳ መከላከያ ወታደር ወደ ደብረማርቆስ እየመጣ መሆኑ ታውቋል፣ ደምበጫን አልፏል።

ጥንቃቄ ይደረግ።
መልዕክቱ ለደብረ ማርቆስ ህዝብ እንዲደርስ እናድርግ!!

 


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE