በሕዝብ ላይ ወንጀል የሰራሁት ጌታቸው አሰፋ አስገድዶኝ ነው ሲል የሶማሌ ክልሉ አብዲ ኢሌ ተናገረ።

በሕዝብ ላይ ወንጀል የሰራሁን ጌታቸው አሰፋ አስገድዶኝ ነው ሲል የሶማሌ ክልሉ አብዲ ኢሌ ተናገረ። አብዲ ኢሌ የክልሉን ፓርላማ አመታዊ ስብሰባ ሲከፍት ባደረገው ንግግር በክልሉ የተፈፀመውን ወንጀል በሙሉ በቀድሞ የደሕንነት ሚኒስትር አቶ ጌታቸው አሰፋ ላይ አድርጎታል።

የቀድሞ ደሕንነት ሚኒስትሩ አቶ ጌታቸው አሰፋ ጭንቅላቴ ላይ ሽጉጥ ደቅኖ የሚያዘኝን ነገር ሁሉ እንድፈፅም ያስገድደኝ ነበር ሲል ፓርላማውን በተለሳለሰ አንደበት አጭበርብሯል።

የቀድሞ ጠቅላይ ሚነስትር ሐይለማርያም ደሳለኝ ባለቤትን ወይዘሮ ሮማንን አግቶ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ያስፈራራና እንደፈለገም ያዘው ነበር ሲል የጌታቸው አሰፋ ወንጀል ካላቸው ውስጥ አንዱን ተናግሯል።

ዶክተር አብይ ኢትዮጵያን ለማዳን ከፈጣሪ የተላኩ ናቸው ።እንደ ዶክተር አብይና ለማ መገርሳ ጥሩና መልካም ሰወች አይቼ አላውቅም ብሏል አብዲ ኢሌ ።

የኔ ስልጣን መልቀቅ በሰፊው እየተናፈሰ ያለው በጌታቸው አሰፋ ተላላኪዎች በኩል ሲሆን ይህን ተገን አድርጎ በክልሉ የገንዘብ ዘረፋ ለማካሔድ ነው ሲል ተናግሯል።

የሕወሓት ሰወች በሕዝብ ላይ ከፍተኛ በደል እንድናደርስ ተጠቅመውብናል ያለው አብዲ ኢሌ ከአሁን በኃላ በይቅር ባይነት ሁላችንም ተደምረን ወደ ልማት ፊታችንን ማዞር አለብን ብሏል

ስብሰባው ነገም ይቀጥላል።

Somali Region parliament starts meeting today. Abdi Iley spoke and here is the key messages in his address:

– All the mistakes I committed is because of Getachew Assefa, former chief of Intelligence
– Getachew Assefa held gun on our head and asked us to do what he wants
– He was the man who held the former PM Hailemariam at gunpoint for 6 years (even at times kidnapping the wife of the former PM)
– Dr. Abiy is sent by God to save Ethiopia
– Dr. Abiy and Lemma Megersa are very good men
– The rumour of my resignation is spread by Getachew Assefa, who wants bags of money as he used to get
– They [Tigres] forced us to do all the things we did
– we need to now forgive everything and move forward

The meeting will continue tomorrow!
Mustafa Omer


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE