ምልአተ ጉባኤው: ለሲኖዶሳዊ ልዩነቱ የመጨረሻ እልባት ለመስጠት ዝግጁነቱን አረጋገጠ፤ አስተዳደራዊ ማሻሻያ በጥናት እንዲፈጸም አዘዘ፤ ነገ ጠዋት መግለጫ ይሰጣል

ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ለዛሬ ማክሰኞ፣ ሐምሌ 3 ቀን 2010 ዓ.ም. የጠራውን አስቸኳይ የምልአተ ጉባኤ ስብሰባ፣ በሲኖዶሳዊው የዕርቀ ሰላም ሒደትና በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ችግሮች ላይ በትኩረት ከተወያየ በኋላ ውሳኔና መመሪያ በመስጠት ማምሻውን አጠናቋል፡፡ ሲኖዶሳዊውን የዕርቀ ሰላም ሒደት በተመለከተ፡- ልኡካን አባቶች፣ እንዳስፈላጊነቱ የሚወስኑበትን ሙሉ ሥልጣን ሰጠ፤ በሠየማቸው 3 ልኡካን አባቶች የመጨረሻ እልባት እንዲያገኝ ወስኗል፤ ለቋሚ ሲኖዶሱ፣ የአካሔድና የሥርዐት …

► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE