በዋሽንግተን የኢትዮጵያ ኢምባሲ የመሸጉ የቀን ጅቦች የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን የአሜሪካ ጉብኝት ላይ ሸፍጥ እያሴሩ ነው

  • በዋሽንግተን የኢትዮጵያ ኢምባሲ በመደረግ ላይ ያለው እሻጥር ካልቆመ በስተቀር የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጉብኝት በሌላ ጊዜ ቢደረግ ይሻላል የሚል አስተያየት በስፋት እየተሰጠ ነው
  • ተቃዋሚውንና ለውጡ የመጣለትን ስደተኛ ኢትዮጵያዊ ሊያስተናግዱ የሚችሉ “በመደመር” መንፈስ የሚያምኑ አዳዳስ ዲፕሎማቶች ዋሽንግተን ውስጥ በአስቸኳይ መመደብ ይኖርባቸዋል።
  • የህወሃት አጀንዳ አራማጅ የኢምባሲ ዝንቦች እንደ መስፍን በዙ፣ ንጉሴ ቢራቱና አሉላ ሰለሞንን የመሳሳሉት ደላሎችን ዲያስፖራው ማየት አይፈልግም
  • የአማራ ህዝብ እንዲወገድለት በሰልፍ ላይ የጠየቀው ስራ ላይ በማዋል ካሳ ተክለብርሃን በአስቸኳይ ከአምባሳደርነት እንዲነሳ ዲያስፖራው እያሳሰበ ነው

በቅርቡ ወደ አሜሪካ በመምጣት ከኢትዮጵያዊያን ጋር ወይይት ያደርጋሉ ተብለው በታላቅ ጉጉት የሚጠበቁትን የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጉብኝት ለማደናቀፍና ለማበላሸት በህወሀት አንጋቾች  ካሳ ተክለብርሃንና ረታ ዓለሙ የሚመራው ኢምባሲ ከፍተኛ አሻጥር በመሸረብ ላይ መሆናቸውን የደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። በአዲስ አበባ፣ በባህር ዳር፣ በወልቂጤ፣ በአርባ ምንጭ፣ በመተከል፣ በእንጅባራና ሌሎችም ከተሞች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን በነቂስ አደባባይ ወጥተው ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ድጋፋቸውን በመግለጻቸው እጅግ ከፍተኛ ብስጭት ውስጥ የወደቁቱና በቅናት የደበኑት ወያኔዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ የግድያ ሙከራ ማድረጋቸው ይታወቃል። በውጭ የሚገኙ የህወሃት አሸርጋጆችም አገሩ ባይመቻቸውም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ደህንነት አደገኛ ሊሆኑ እንደሚችሉ መገመት አያዳግትም።

በአጭር ጊዜ ውስጥ ታላላቅ ለውጦችን እያመጡ ለሚገኙት ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በአገሪቱ ማዕዘናት የሚኘው ህዝብ ድጋፉን እንዳይሰጥ የተለያየ መሰናክሎችን በመፍጠር ላይ የሚገኙት ወያኔዎች አስቀድመው በየኢምባሲው ውስጥ በሰገሰጓቸው ካድሬዎቻቸው አማካይነት ህዝብ ላይ የሚሰሩትን ወንጀል አሁንም ቀጥለውበታል። ወያኔዎች ህዝብ ያስተላለፈው “በቃችሁ ተውን” የሚለው መልዕክት ሊገባቸው አልቻለም። የቀን ጅቦቹ ተጠራርገው ካልተወገዱ በስተቀር ህዝብ ያደረገላቸውን ይቅርታ እንደሞኝነት በመቁጠር አሁንም መሰሪነታቸውን አልተውም፣ ሊተውም አይችሉም።

የህወሃቱ ተላላኪ ረታ አለሙ ከህወሃት የቀን ጅቦች በቀጥታ በሚደርሰው መመሪያ እረብሻና ብጥብጥ እንዲፈጠር በማድረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የአሜሪካ ጉብኝታቸው እንዲከሽፍ እርብርቦሽ እያደረገ መሆኑን ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ ከኢምባሲው አካባቢ ያሉ ውስጥ አወቆች እየተናገሩ ነው። ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የከረረ ጥላቻ ያለውና በየሚዲያው የሚያብጠለጥላቸውና  ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከትግራይ ህዝብ ጋር ለማጣላት በሙሉ ሰዓቱ የሚንቀሳቀው የህወሃቱን ቱባ ካድሬ አሉላ ሰለሞንና እንዲሁም በህዝብ የተተፉት ነባር የወያኔ ወጥ ቀማሾች እነ ንጉሴ ወ/ማ፣ መስፍን በዙ፣ ቅድስት አቤነዘር፣ ዶክተር በላይ፣ ንጉሴ ቢራቱና መሰሎቻቸው መድረኩን እንዲቆጣጠሩና የለውጡ ደጋፊዎች እንዳይሳተፉ አሻጥር እየሰሩ ይገኛሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የጀመሩትን ለውጥ ለማኮላቸትና የህዝብን ተስፋ ለማጨለም ህወሃት የንጹሃንን ደም ከማፍሰስ ጀምሮ የተለያዩ ወንጀሎችን እየፈጸመ እንደሚገኝ በመረዳት  በተለይም በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ውስጥ የማጽዳት እርምጃ በፍጥነት በመውሰድ ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጡና ህዝብን የሚያከብሩ አዳዳስ ዲፕሎማቶች መመደብ ይኖርባቸዋል። የነቀዙና የበሰበሱ ህወሃትን እንጅ ህዝብን አገልግለው የማያውቁ እንደ ረታ አለሙ የመሳሰሉ ተባዮች ጊዜ ሳይባክን መወገድ ይገባቸዋል። ከአንድ ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊ ይኖርበታል በሚባለው አሜሪካ ውስጥ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የተጀመረውን ለውጥ ከልብ የሚደግፉና ከህወሃት ጋር ንክኪ የሌላቸው ኢትዮጵያን እንደ አገር መወከል የሚችሉ የህዝብ አገልጋይ ዲፕሎማቶችን መመልከት ዲያስፖራው ለረዥም ዓመታት ናፍቋል።  ለሰብዓዊ መብት መከበር፣ ለዲሞክራሲ፣ ለአገር አንድነትና ለህዝብ እኩልነት ለ27 ዓመታት ቁርና ሀሩር ሳይበግራቸው የጮሁ  በአሜሪካ የሚገኙ ወገኖች የጠቅላይ ሚኒስትሩን የመቀበልና የማስተናገድ ኃላፊነት መያዝ ይኖርባቸዋል እንላለን።

ይህንን አስመልክቶ “ሹክሹክታ” በሚባለው ዩቱብ ቻናል የተለቀቀውን ለግንዝቤ እንዲረዳ አቅርበንላችኋል።

 


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE