በሶማሌ ክልል አምባገነንነት እንዲሰፍንና ኢሰብዓዊነት እንዲስፋፋ ያደረጉ ባለስልጣናትን ማስወገድ ተጀምሯል።

 

ኢሰብዓዊና ዘራፊ ባለስልጣናትን በጊዜ ማስወገድ ለሐገር ሰላም ይበጃል።

በሶማሌ ክልል አምባገነንነት እንዲሰፍንና ኢሰብዓዊነት እንዲስፋፋ ያደረጉ ባለስልጣናትን ማስወገድ ተጀምሯል። ከሕወሓት ጄኔራሎች ጀምሮ በፌዴራሉ መንግስት የሕወሓት ባለስልጣናት እስከሚደገፈው የአብዲ ኢሌ የሰቆቃ ሰንሰለት ድረስ መበጣጣስ ተጀምሯል።

በክልሉ በሰው ልጆች ላይ ከሚደረግ ኢሰብዓዊ ድርጊት ጀምሮ እስከ ሃገር ኢኮኖሚ ጉዳት ድረስ ከፍተኛ ወንጀሎች በመንግስት ባለስልጣናት ይፈጸማሉ። ይህ አደገኛ አካሔድ ሕዝብንና አገርን እየጎዳ ስለሚገኝ የዶክተር አብይ አስተዳደር ተግባራዊ የማጥራትና የማስወገድ ስራውን በይፋ ጀምሯል። ሜጄር ጄኔራል አብርሃ (ካርተር) ከስልጣኑ የተሰናበተ ሲሆን በቀጣይነት የሶማሌ ክልል ምክር ቤት ኢሰብዓዊ ድርጊት የፈጸሙትን ለማባረር ከስልጣን ለማንሳት አስቸኳይ ስብሰባ የጠራ ሲሆን የሕወሓት ባለስልጣናት ሶማሌ ክልል እንገነጠላለን በሉ የሚል ጫና በመፍጠር ላይ መሆኑ ተሰምቷል።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE