የሰሜን ሱዳን ሰራዊት በድጋሚ የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ ገብቷል።

የሱዳን ሰራዊት ዛሬም ወረራ ፈፅሟል

ተስፋፊው የሰሜን ሱዳን ሰራዊት ዛሬ ሐምሌ 3/2010 ዓም የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ ገብቷል። በትናንትናው ዕለት በአማራ ገበሬዎችና በአካባቢው ሚሊሻ ወደመጣበት የተመለሰው የሱዳን ጦር ራሱን አጠናክሮ ዛሬ ሐምሌ 3/2010 ዓም ከቀኑ 8: 30 አካባቢ የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ ገብቷል ተብሏል።

በትናንትናው ዕለት በርካታ ሚሊሻ አባላት ድንበሩን በመጠበቅ ላይ የነበሩ ቢሆንም ዛሬ ከ12 የማይበልጡ የሚሊሻ አባላት ብቻ እንደሚገኙ ገበሬዎቹ ገልፀውልኛል።

የሱዳን ሰራዊት አባላትና የአማራ ገበሬዎች ኮር ሁመር የሚባል ከተማ ወጣ ብሎ የሚገኝ ቦታ ላይ ቦታ ይዘው እንደሚገኙ ገበሬዎቹ በስልክ ገልፀውልኛል። በአካባቢው ገበሬዎችን የሚያግዝ ሌላ የመንግስት ሀይል እንደሌለ ለማወቅ ተችሏል።

ትናንት ሀምሌ 2/2010 ዓም የሱዳን ጦር በከባድ መሳርያ የታገዘ ወረራ ፈፅሞ በገበሬዎቹና በሚሊሻው ወደመጣበት እንዲመለስ ተደርጓል። በወቅቱም 3 አባላቱ ቆስለውበታል። በዛሬው እለትም በከባድ መሳርያ ታግዞ ድንበር እንደተሻገረ ገበሬዎቹ ገልፀዋል።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE