የአየር ኃይል የጦር ጄት አብራሪ ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ከኤርትራ እስር ቤት መፈታቱ ዜና ስህተት መሆኑ ተገለፀ

በትላንትናው እለት በኤርትራ ፕሬስ ፈስቡክ ፔጅ ላይ ስለካፕቴን በዛብህ ፔጥሮስ ከኤርትራ እስር ቤት መፈታት የሚገልጸው ዜና እዚህ ዌብሳይት ላይ ቀርቦ ነበር። ዜናው ስህተት መሆኑን አረጋግጠናል።

ኤርትራ ኢትዮጵያውያን እስረኞችን ትፈታለች የሚለውን ግምት ተከትሎ ለ20 ዓመት ኤርትራ ውስጥ ታስሮ የነበረው የአየር ኃይል የጦር ጄት አብራሪ ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ከእስር ተፈቷል የሚሉ ዘገባዎች በተለያዩ ዌብሳይቶች ላይ ቀርበዋል።

በባድመ ውጊያ ከ20 ዓመት በፊት በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት የሚያበረው የጦር ጀት ተመቶ በኤርትራ ወታደሮች እጅ ከወደቀ በኃላ ታስሮ ዛሬ ዶ/ር አብይ ከእስር እንዲፈታ አድርገውታል ተብሎ ነበር።

ካፕቴኑና ሌሎችም በኤርትራ እስር ቤቶች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ያሉበት ሁኔታ ግልጽ አይደለም። ተጨማሪ መረጃ እንዳገኘን እንዘግባለን።

በዛብህ ጴጥሮስ የፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ወንድም ነው።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE