የአማራ ገበሬ የሱዳንን ዳግም ወረራ አሳፍሮ መልሷል

የአማራ ገበሬ የሱዳንን ዳግም ወረራ አሳፍሮ መልሷል

ትናንት የሱዳን ጦር በአብደራፊና በኮረደም አጠገብ ኮር ሁመርደ የተሰኘች ከተማ አቅራቢ ወደከውሊ የተባለ የኢትዮጵያ ግዛት ወርሯል። ሆኖም ሕዝብና ሚሊሻ ባደረጉት መከላከል የሱዳን ጦር ተሸንፎ ተመልሷል። የሱዳን ጦር 6 የአር ፒጅ ከባድ መሳርያዎችን በሕዝብ ላይ ተኩሷል። ሆኖም ጉዳት እንዳላደረሰ ለማወቅ ተችሏል።

በሌላ በኩል ግን ሶስት የሱዳን የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከገበሬውና ሚሊሻ በተተኮሰ ጥይት መቁሰላቸው ተገልፆአል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በአቅራቢያው የነበር ቢሆንም “ትዕዛዝ አልተሰጠኝም” ብሎ የሱዳንን ዳግም ወረራ ዳር ቆሞ ተመልክቷል። የአማራ ልዩ ሀይል ዘግይቶ የደረሰ ሲሆን “ተመለስ” ተብሎ መመለሱን ምንጮች ገልፀዋል። በድንበር አካባቢ ገበሬውን እያገዙ የሚገኙት ሚሊሻ ሲሆኑ ትናንት ከ1000 በላይ የሚሊሻ አባላት በድንበር አካባቢ እንደነበሩና የአማራ ገበሬዎች የሱዳንን ጦር ወደመጣበት ሲመልሱ ትልቅ እገዛ ማድረጋቸው ተገልፆአል። የፌደራልም ሆነ የክልሉ መንግስት ሉአላዊነት ማስከበሩን ግዴታ አሁንም ለአማራ ገበሬዎች እንደጣሉት ነው።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE