ጊንር ውስጥ እሥረኞችና ፖሊሶች ለኮሮናቫይረስ ተጋለጡ

በምሥራቅ ባሌ ዞን ጊንር ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ተይዘው የነበሩ ቁጥራቸው ወደ ሃምሣ የሚጠጋ ሰዎች ለኮሮናቫይረስ መጋለጣቸው ተነግሯል።

ስለሁኔታው ለቪኦኤ ማረጋገጫ የሰጠው የምሥራቅ ባሌ ዞን አስተዳደር ከተጋላጮቹ ጋር ቅርበትና ንክኪ የነበራቸውን ሰዎች እየተከታተለ መሆኑን እና ሌሎች እስረኞች እንዳይጋለጡ ለመከላከል እየሠራ መሆኑን ገልጿል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።