ሕወሃት ለኢትዮጵያ አሁናዊ የፖለቲካ ምስቅልቅል ምክንያት ነው


ኢትዮጵያን ካጋጠሟት እጅግ ውስብስብ ችግሮች ለማዳን የተለያዩ ጠቃሚ ሃሳቦችን እና ገንቢ ትችቶችን የሚያቀርቡ ነፃ ሚዲያዎች ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ይታወቃል። ስለዚህም ኢትዮ360፣ መረጃ ቲቪ፣ አዲስ ድምጽ፣ ምንሊክ ቲቪ እና ሌሎችም የኢትዮጵያዊነት አጀንዳ የሚያራምዱ ሚዲያዎች በመተባበር ፕሮግራሞቻቸውን በሳተላይት ቲቪ ለኢትዮጵያ ህዝብ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ሚዲያዎች የፈጠሩት ማህበር የሳተላይት ወጪውን መሸፈን እንዲያስችለው ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ ከፍተናል → እዚህ ሊንክ ላይ ይጫኑ። ለትብብርዎ እናመሰግናለን።
ሕወሃት ለኢትዮጵያ አሁናዊ የፖለቲካ ምስቅልቅል ምክንያት ነው …የትግራይ ተወላጅ ፖለቲከኞች
ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ለኢትዮጵያ አሁናዊ የፖለቲካ ምስቅልቅል ምክንያት እንደሆነ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ፖለቲከኞች ገለፁ።
Image may contain: 2 people, people sitting and hatኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የትግራይ ዴክራሲያዊ ፓርቲ (ትዴፓ) አመራሮች ”በትግራይ ክልል ያለው የዴሞክራሲ ምህዳር ተዘግቶ ከሕወሓት ውጭ አማራጭ ሃሳብ ማቅረብ ወንጀል ተደርጓል” ይላሉ።
የትዴፓ ምክትል ሊቀመንበር አቶ መስፍን ደሳለኝ ክልሉ የሕወሃት ተቃዋሚዎች በባንዳነት የሚፈረጁበት፣ የሚሳደዱበትና የሚታሰሩበት እንደሆነ ገልጸዋል።
የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሙሉብርሃን ሃይሉ ክልሉ መንግስትና ፓርቲ ያልተለየበት፣ አማራጭ ሃሳብ ማንሳት የማይቻልበት ፖለቲካ ሁኔታ ተባብሶ የመቀጠሉን ሃሳብ ይጋራሉ።
የሕወሃትን አስተሳስብ የሚቃወሙ የትዴፓ አባላት ተለይተው እየተሳደዱና እየታሰሩ እንደሆነ አንስተዋል።