ሀይቅ ከተማ ከፍተኛ ተቃዉሞ ተቀስቅሷል

ሀይቅ ከተማ ከፍተኛ ተቃዉሞ ተቀስቅሷል፣ በርካታ የአካባቢዉ ወጣቶች ወደ ተቋማት በመግባት ባንድራዎችን እያወረዱ ቀይረዋል!፣ ከአዲስ አበባ ወደ ትግራይ የሚሄደዉ ዋና መንገድ ተዘግቷል፣
በርካታ ፌዴራል አከባቢዉን ወረዉታል። የተወሰኑ የክልሉ ፅጥታ አስከባሪዎች ጉዳት ደርሶባችዎል። በጣም ብዙ ወጣቶች እርህራሄ በሌላችው ልዩ ሃይሎች ተደብድበዋል። ከድብደባው ባሻገር የተያዙ ወጣቶችም አሉ። በድብደባው የተጎዱ ወጣቶች በአንቡላንስ ወደ ደሴ እየሄዱ ነው። አሁንም አከባቢው ያልተረጋጋበት ሁኔታ ነው ያለው። ተጨማሪ ልዩ ሃይል በአይሱዚ ከደሴ ወደ ወደ ሃይቅ እየመጣ እንደሆነ ለማዎቅ ተችሎል።

“የተሁለደሬ ወረዳና የሀይቅ ከተማ ህዝብ ባለፈው ቅዳሜ በቀን 23/10/2010 ዓ.ም በጋራ እየመጣ ያለውን ለውጥ እውቅና ለመስጠትና የአማራን ህዝብ መሰረታዊ ጥያቄዎችን ለማሳወቅ ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይወጡ ሰይድ ሀሰን (የተሁለደሪ ወረዳ አስተዳዳሪና የግብርና ሀላፊ) እና ታደሰ ወ/ማርያም(የሀይቅ ከተማ ከንቲባ) የተባሉ ከከተማ እስከ ገጠር ቀበሌ ድረስ በመዝለቅ ሆድ አደር የሆኑ ግለሰቦችን በማደራጀትና ተልእኮ በመስጠት እንዳይሳካ ቢጥሩም ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ አቋሙን አንፀባርቋል።

ነገር ግን በስተመጨረሻ ቢሻናቆ የሚባል ሰፈር ላይ የእነዚህ ግለሰቦች ታጁ የሚባል ካድሬ 7 ሚሊሻ ይዙ ወጣቱን እንድጨርስ ቢሞክርም መተኮስ እንደጀመሩ በህዝብ ቁጥጥር ስር ውሏል። እስካሁንም በህግ ቁጥጥር ስር ይገኛል።

ዛሬ ደግሞ በቀን 28/10/2010 ዓ.ም የተሁለደሬ ወረዳ ምክር ቤት አባላት 4ኛ ዙር ጉባዔ እያደረጉ ባለበት ሰዓት ወጣቱ እነዚህ ሰወች ከስልጣን ይነሱ ሌቦች ናቸው በማለት ወደ ምክር ቤቱ ተሰብሳቢወች ሲገቡ ወደ ግርግር በመቀየሩ የመለስ ፓርክን አውድመውታል። በተጨማሪም በየፅ/ቤቱ በመዙር ትክክለኛውን ሰንደቅ ዓላማ ቀይረዋል።
አሁንም ህዝቡ ወጥቶ አደባባይ ላይ ይገኛል አቶ ገዱ መጥቶ ያናግረን እያሉ ነው። በአሁኑ ሰዓት ልዩ ሀይል ወደ ከተማዋ በመግባት ላይ ነው።”