በኮንሶ ዞን እና በአሌ ልዩ ወረዳ በተከሰተ ግጭት 11 ሰዎች ሲሞቱ 20 ሺህ ተፈናቀሉ

በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በሚገኙት በአሌ ልዩ ወረዳ እና በኮንሶ ዞን መካከል በመሬት ይገባኛል ተነስቶ ለቀናት በቀጠለ ግጭት ቢያንስ የ11 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ከ20 ሺህ በላይ ሰዎች ከመኖሪያቸው መፈናቀላቸው ተነግሯል። በአሁኑ ወቅት የፌደራልን የክልሉ የጸጥታ ኃይሎች ወደ አካባቢዎቹ መሰማራታቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገልጸዋል።…