የሕዳሴው ግድብ በቀጠናው መገንባቱ የጎላ ጥቅም ይኖረዋል ሲል ጥቁር የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት ስብስብ ገለጸ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ጥቁር የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት ስብስብ (Congressional Black Caucus) የህዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ የጎላ ጥቅም ያለው ፕሮጀክት መሆኑን ገልፆ ሀገራቱ በውይይታቸው ወቅት ከአፍሪካ ህብረት ጋር ብቻ ምክክር እንዲያረጉ መክሯል!

ስብስቡ ባወጣው መግለጫ ሀገራቱ በግድቡ ዙርያ የሚያደርጉት ውይይት እኩል ተጠቃሚነትን፣ ቅን ልቦናን እና አለም-አቀፍ ህግን መሰረት ያረገ መሆን አለበት ብሏል።

“ግድቡ በቀጠናው መገንባቱ የጎላ ጥቅም ይኖረዋል፣ ስለዚህ ይህ ስብስባችን በ2015 በሀገራቱ የተፈረመው ስምምነት እንዲከበር አሜሪካን እና ሌሎች አለም-አቀፍ ተቋማትን ያሳስባል” ብሏል መግለጫው።

መግለጫው አክሎ “በሰላማዊ መልኩ የሚጠናቀቅ እና ሁሉንም የሚጠቅም ስምምነት እንዲኖር የአፍሪካ ህብረት ትልቅ ሚና ሊጫወት ይገባል። ግድቡ የምግብ እጥረትን ለመከላከል፣ ኤሌክትሪክ ለብዙዎች ለማዳረስ፣ የመጠጥ ውሀ ለማስፋፋት እንዲሁም በአካባቢው ያሉ ሀገራትን ኢኮኖሚ ለማሳደግ ትልቅ ሚና ይኖረዋል ” ብሏል።

ልክ የዛሬ ወር ገደማ አሜሪካዊው የመብቶች ተሟጋች ጄሲ ጃክሰን ግብፅ ለተ.መ.ድ የፀጥታው ምክር ቤት ያስገባችው የመጀመርያ ደብዳቤ ላይ ጥቁር የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት ስብስብ ተቃውሞ እንዲያሰሙ ጥሪ አቅርቦ ነበር። ጄሲ ጃክሰን በወቅቱ ግብፅ የአሜሪካ መንግስትን፣ የአለም ባንክን እንዲሁም ተ.መ.ድን በመጠቀም የቅኝ ግዛት ውል በ11 የአፍሪካ ሀገራት ላይ ለመጫን እየሞከረች ነው ብሎ ነበር። Elias Meseret

ጥቁር የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት ስብስብ ያወጣው መግለጫ: 

The Congressional Black Caucus Statement on the Ethiopian Renaissance Dam

https://cbc.house.gov/news/documentsingle.aspx?DocumentID=2200