በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 በሽታ ያለበት ሰው ላይ ቫይረሱን ለመለየት የሚረዳ የሞለኪዩላር ምርመራ እንደሚካሄድ ታወቀ።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የኮቪድ-19 አንቲቦዲ (Antibody) የቅኝት ዳሰሳ አስመልክቶ የወጣ መግለጫ

በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ምርመራ ከጥር 29 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ የተጀመረ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በሁሉም ክልሎች በሚገኙ ላቦራቶሪዎች እስከ ሰኔ 14 ቀን 2012 ዓ.ም 216¸328 ምርመራ ተደርጓል። ይህ የምርመራ አይነት የኮቪደ-19 በሽታ ያለበት ሰው ላይ ቫይረሱን ለመለየት የሚረዳ የሞለኪዩላር ምርመራ ነው።

ከዚህ በተጨማሪ በማህበረሰብ ውስጥ ያለውን የበሽታ ስርጭት ለመረዳት (surveillance) እና በአንጻሩ ምላሽ ለመስጠት እንዲሁም ይበልጥ ተጋላጭ በሆኑት የማህበረሰባችን ክፍሎች ላይ ያለውን የኮቪድ-19 በሽታ ስርጭት ለማወቅ የሚረዳ አንቲቦዲ ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑ ይታመናል፡፡ ይህ የአንቲቦዲ የቅኝትና ዳሰሳ ምርመራ አይነት በአገራችን ለምርምር ለመጠቀም እና ከላይ የተጠቀሱትን ዓላማዎች ለማሳካት ከሰኔ 15 እሰከ ሀምሌ 7 ቀን 2012 ድረስ በሀገራችን የሚካሄድ ይሆናል።

አንቲቦዲ ማለት ሰውነታችን ለበሽታ በሚጋለጠበት ወቅት ለበሽታው ከተጋለጠ ከአንድ እስከ ሶስት ሳምንት ድረስ በሽታውን ለመከላከል ሰውነታችን የሚያመርታቸው የበሽታ ተከላካዩች ናቸው፡፡ በሰውነታችን ውስጥ የአንቲቦዲ መመረት በእድሜ፣ የአመጋገብ ሁኔታ፣ የምንጠቀማቸው መድሁኒቶች፣ የበሽታው ከባድነት እና ተጓዳኝ በሽታዎች ላይ ይወሰናል፡፡ ምርመራው ከሰውነታችን ከ3-5 ሚሊ ሊትር ደም ናሙና በመውሰድ የሚደረግ ሲሆን የበሽታው ተከላካዮች (አንቲቦዲ) እንደየበሽታው ዓይነት የሚለያዩ ሲሆን ምርመራው ኮቪድ-19 ለመካላከል እና ለ መቆጣጠር ለሚደረገው የቅኝት ዳሰሳ ውጤታማነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው፡፡ ነገር ግን የአንቲቦዲ ምርመራ ውጤትን ብቻ ተጠቅሞ ህክምና መስጠት አይቻልም፡፡

ይህ የቅኝት ዳሰሳ በሀገራችን ያለውን የኮሮና ቫይረስ በሽታ (ኮቪድ-19) ስርጭት ለማወቅ ከሰኔ 15 ቀን 2012 ጀምሮ በአዲስ አበባ፣ ድሬደዋ ከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ በሁሉም ክልሎች ይካሄዳል፡፡ በመሆኑም ህብረተሰቡ፣ የጤና ባለሙያዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ለትግበራው አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን [email protected] በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡

ሰኔ 15 ቀን 2012 ዓ.ም

የጤና ሚኒስቴር