የድህነት እና የተስፋ መቁረጥን ዑደትን ለመሻር ሀብታችንን ማሰባሰብ እንችላለን፡፡ ጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ

“የድህነት እና የተስፋ መቁረጥን ዑደትን ለመሻር ሀብታችንን ማሰባሰብ እንችላለን፡፡” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ
በሶማሊያ እና በሶማሌላንድ ግንኙነት ዙሪያ በተደረገው የምክክር ጉባዔ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ዕርቅን ማውረድ ለቃጣናው ውሕደት መሠረት እንደሆነ ገልፀዋል። የምክክር ጉባኤው በየካቲት 2012 በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ አዘጋጅነት በአዲስ አበባ የተደረገው ውይይት ተከታይ ክፍል ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር እንዳመለከቱትም ትብብር እና ሰላም በግንባር ቀደምነት ከተተገበሩ ውጤታማ በሆነ መንገድ የቀጣናውን ልማት ለማረጋገጥ የሚያስችል የተትረፈረፈ ሀብት አለ።
የቀጣናው ሰላም ከተረጋገጠና በትብብር ከተሠራ “የድህነት እና የተስፋ መቁረጥን ዑደትን ለመሻር ሀብታችንን ማሰባሰብ እንችላለን” ብለዋል ዶክተር ዐብይ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በሴማሊያና ሶማሌላንድ ግንኙነት ዙሪያ በሚደረገው ውይይት ለመሳተፍ ዛሬ ረፋዱን ወደ ጂቡቲ ማቅናታቸው የሚታወስ ነው፡፡