የአፍሪካ ኅብረቱ መስጊድ እና ሕጋዊነቱ

የቦታው አሰጣጥ፥ በሃይማኖት ተቋማት የአምልኮ ማካሔጃ ቦታ አፈቃቀድ መመሪያ ከተዘረዘሩት መሳፍርት አንዳቸውንም አያሟላም፤ ከነባሩ ደብር 100 ሜትር በማይርቅ ቦታ መስጊድ እንዲተከል መፍቀድ፣ የእምነት ነፃነትን መጋፋት እንጂ ማስከበር ሊኾን አይችልም፤ የከተማዋን ማስተር ፕላንም የተከተለ አይደለም፤ ደብሩ በልማት ስም ለተወሰደበት ቦታ ትክ ሳይሰጥ ከማስተር ፕላኑ ጋራ በሚጋጭ መልኩ ለሌላው መፍቀድ አግባብ አይደለም፤ “ለልማት ይፈለጋል” በሚል ብዙኃን ምእመናን …