መርካቶ ምእራብ ሆቴል አከባቢ አንድ የባንክ ሰራተኛ በኮሮና መያዛቸው በባንኩ ሰራተኞች ላይ ድንጋጤ ፈጥሯል

ምዕራብ ሆቴል አካባቢ የሚገኝ የአንድ ባንክ ሰራተኛ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተከትሎ በባንኩ ሰራተኞች ላይ ከፍተኛ ድንጋጤ ተፈጥሯል

የጥበቃ ሰራተኛ የሆኑት ይህ ሰው የአብነት አካባቢ ነዋሪ ሲሆኑ ለምርመራ ናሙና ሰጥተው እንደነበርና ናሙና መስጠታቸውን ሳይናገሩ እስከዛሬ ጠዋት ድረስ በስራ ገበታቸው ላይ እንደነበሩ የባንኩ ሰራተኞች ለናፍቆት ሚዲያ ገልፀዋል::

የባንኩ ሰራተኞች እንደሚሉት የየባንኩ የጥበቃ ሰራተኛ በቫይረሱ መያዛቸውን የናሙና ውጤታቸው ያረጋገጠ ሲሆን የጤና ቢሮ ሰዎች ሰውየውን ለመውሰድ መጥተው የነበረ ሲሆን ሰውየው ስራ አድረው ዛሬ ጠዋት ወደቤታቸው መሄደቸውን ሰራተኞቹ ገልፀውልናል:: ይህን ተከትሎ ባንኩ ወዲያው በሩን ዘግቶ የሚሆነውን ሲጠብቅ የነበረ ሲሆን በሗላም የባንኩ ሃላፊዎች ሰራተኞቻቸውን ከ14 ቀን በፊት ወደስራ እንዳይመጡ ነግረው ማሰናበታቸውንም ምንጮቻችን ገልፀዋል::

በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ በማህበረሰብ ደረጃ ስርጭት መጀመሩንና የዚህም ማሳያው አብዛኞቹ ተጠቂዎች የጉዞ ታሪክም ሆነ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ የሌላቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ህክምና ሳይንስ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ተግባሩ ይግዛው የዛሬው አዲስ አድማስ ላይ ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል!!

ናፍቆት ሚዲያ