የህዝብን ፍላጎት መሰረት በማድረግ በኢትዮጵያ የተጀመረው ፈጣን ለውጥ ተጨባጭ ስኬቶችን በማስመዝገብ ላይ ነው

ባለፉት ጥቂት ወራት መንግስት ሀገራዊና ከባቢያዊ ሁኔታዎችን ታሳቢ በማድረግ እየወሰዳቸው ያሉት እርምጃዎች ፈጣንና ተጨባጭ ውጤቶች በማስመዝገብ ላይ እንደሚገኙ ተገለፀ። የህዝብን ፍላጎት መሰረት በማድረግ በኢትዮጵያ የተጀመረው ፈጣን ለውጥ ተጨባጭ ስኬቶችን በማስመዝገብ ላይ እንደሆነ እና ለውጡን ማንም ሊያቆመው በማይችለው ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የፌዴራል የመንግስት ኮሙዩንኬሽን ባወጣው መገለጫ አስታውቋል።

በዚህ መሰረት የህግ ታራሚዎች በይቅርታ ከእስር ተለቀዋል፣ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር መልካም ግንኙነትን መፍጠር ተጀምሯል፣ በትጥቅ ትግል ላይ የተሰማሩ ሃይሎችም ሰላማዊ የትግል መስመርን ተቀላቅለዋል፣ ከኤርትራ ጋር የነበረው ሞት አልባ ጦርነትም መቋጫ በማግኘት እንደሆነና ሌሎች ህብረተሰቡ ሲያነሳቸው የነበሩ በርካታ ጥያቄዎች ምላሽ እየሰጠ መሆኑን በመግለጫው አመልክቷል።

ይሁን እንጂ የህዝንቡን ለውጥ መንገድ ለማደናቀፍና የሂደቱን አቅጣጫ ለማስቀየር ጥረት በማድረግ ላይ እንደሆነ ተመልክቷል። መንግስትም ጉዳዩ በጥልቀት የሚመረምርና የመፍትሄ ሃሳብ የሚያቀርብ ኮሚቴ አቋቁሞ እየሰራ በመሆኑ ማንኛውንም ዜጋ ለኮሚቴው ተገቢውን መረጃ በመስጠት እንዲተባበር ጥሪውን አቅርቧል።

(ኤፍ.ቢ.ሲ)