ኢትዮጵያውያን ሁሉ ልንሰማው የሚገባን ዓመታዊ ትምህርት፤ በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

ቀሲስ አስተርአየ ዘመናችን እንዳፈራቸው ሰባኪዎች ከድርጅት ትርፍ ከሰው ምስግና ለማግኘት የፖለቲካውን ዝንባሌ እያነበቡ፤ የህዝብ ስሜት ሲግል እየጋሉ፤ ሲበርድ እየበረዱ እንደ ጠፍ ጨረቅ በዓውደ ምህረት ላይ ብቅ የሚሉ ሰባኪ አይደሉም። እራሳቸውና ጥቅማቸው የማይናከበትን መንገድ እየመረጡ የህዝቡን ወቅታዊ ስሜት እያከኩ  በመስበክ ሴቱን እልል በሉ፤ ወንዱን አስጨበጭቡ ሲሉ ተሰምተው አያውቁም። በከንሳስ መድኃኔዓለም አውደ ምህረት ላይና፤ በሌሎችም መገናኛ መስመሮች  ያለማቋረጥ ያቀረቧቸው መልእክቶች በቤተ ክርስቲያናችን በአገራችን ላይ የሚደረገውን ግፍ እየገለጹ ህሊናውን ረስቶ ለሆዱ ተገዥ የሆነውን ሁሉ የሚገርፉ ናቸው።

የሚያቀረቧቸው መልእክቶች የቀደሙ ሊቃውንት አበው ይጠሩባቸውን የነበሩትን የእውቀት የሞራልና የእምነት ስሞች ደራርበው በመሸከም ህዝብ የሚያታልሉትን አስመሳዮች  እያጋለጡ፤  የቀደሙ ሊቃውንት አበው ይለብሷቸው የነበሩትን የክብር ካባዎች ደራርበው የለበሱትን እየገፈፉ በህዝብ ፊት ራቁታቸውን የሚያቆማቸው ሁሉ የሚወረወሩባቸው ዘለፋ ሳይበግሯቸው፤ መከራን ከመከራ፤ ዘመንን ከዘምን፤ ትውልድን ከትውልድ፤ የቀደሙ ካህናትን ከዘመኑ ካህናት ጋራ እያነጻጸሩ ስለ አገራችንና ቤተ ክርስቲያንችን የታያቸውን  ገልጸው ሳይናገሩ ያለፉበት ወቅት የለም።

በመከራው ዘመን በያመቱ ለሚታሰበው ደብረ ዘይትን የኢየሱስ መፈክር  ወይም ፍካሬ ኢየሱ በሚል ርእስ በጽሁፍም በቪዲዮም አቅርበዋል።  ራእይ የማያሳይና  ወደ ተግባር የማይመራ ከጾም ጋራ ተያያዞ የሚደረግ ሱባዔም ከማታልያና መስመሩን ስቶ ህዝብ ከማሳት የራቀ መሆኑን ለማሳየት  የዘንዶ ሱባዔ በማለት አቅርበውልን ነበር።  የበለጠ ማወቅ ከፈለጉ  https://ecadforum.com/Amharic/wp-content/uploads/2014/08/yezendow-subae.pdf?x46017 የሚለውን ቢጫኑ የዘንዶውን ሰባዔ ሊረዱ ይችላሉ።

የዋልድባ ገዳም መነኮሳት ይፈቱ ብለው እንዲጮኹ በሚያስገድደው በመንበረ ፓትርያርክ ላይ የተቀመጡት አባ ማትያስ፤ መነኮሳቱ መታሰራቸው እንዳነገር ከማፈናቸው ባሻገር፤ ገዳሙን ለመዘበረው መነኮሳቱን ላሰረው ለወያኔው ተላላኪ ሆኖ  አገር እየቆረሰ ህዝብ እየከፋፈለ ፤ ለክብራቸውና ለህልውናቸው የሚታገሉትን ትውልድ (ቄሮ ፋና ) ለአገራችን ለክብራችን የምናደርገውን ትግል አይደገመንም እያሰኘ፤  ላስገደለው ለአቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ሽልማት ሰጥተዋል። ለአቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ሽልማት መስጠታቸውም በእለቱ ምንባብ  በማቴ ወንጌል 24፡15 ላይ ኢየሱስ እንዳመለከተው፤ በቤተ ክህነቱ ዙሪያ የተኮለኮሉት የወያኔን የጥፋት ርኩሳት ለመፈጸም የተሰለፉ መሆናቸውን በዘንድሮው ደብረ ዘይት ባቀረቡት ትምህርት አሳይተውናል።

ቀሲስ ባቀረቡት በዘንድሮው ትምህርት “ይህ ቀን አንድ ሰው ከአዳኝ አንበሳ ሲሸሽ፤  ድብ እንዳጋጠመው፤ ከድቡም አምልጦ ከቤቱ ደርሶ የቤቱን ግርግዳ ተደገፎ አረፍኩ ሲል፤ በቤቱ ግድግዳ ዘልቃ የገባች  እባብ ነድፋ ገደለችው” 5፡19 ብሎ  ነቢዩ  አሞጽ ከተናገረ ተነስተው ፤  መላከ ብርሀን አድማሱ ጀንበሬ ከ80 ዓመት በፊት በጣሊያን ወረራ ዘመን ያቀረቡትን ቅኔ እንደማስረጃ ተጠቅመው፤ በከንሳስ መድኃኔዓለም አውደ ምህረት ላይ ያቀረቡት ትምህርት፤ የኢትዮጵያን ህዝብ ለመደምሰስ የሚመጣ ጠላት ሁሉ አስቀድሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ እንደሚዘምትና፤ ይህን በመሰለ አስከፊ የመከራ ዘመንም እንደ መላከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ የመሳሰሉ ሊቃውንት  ያፈራች ባለውለታ ቤተ ክርስቲያን እንደሆነች አሳይተዋል።

በቤተ ክርስቲያናችን ከፍተኛው ትምህርት ተኮትኩተንና  ተቀርጸን አድገናል የምትሉ ካላችሁ፤ የራሳችሁን ስሜትና ህሊና ትፈትሹበትና ራሳችሁንም ትታዘቡበት ዘንድ ቀሲስ ካቀረቡት ትምህርት በፊት ባምስቱ የመከራ ዘመን  መላከ ብርሀኑ አድማሱ የተቀኙትን ቅኔ  ከዚህ በታች አቅርበንላችኋል።

የመላከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ ቅኔ እነሆ

አመ ወርኀ ዘርእ ንዝራእ ዘአመ ማእረር ንዘርእ፤ ሰቆቃወ መስተገብራን ውሉደ ህሬ።

ዘአመ ማእረር ይዘርእ እስመ ኢይረክብ  ፍሬ፤

ወዮም ውእቱ ዘመዋዕለ ዘርዕ  ፍካሬ፤

ወዳግመ ምጽአተ አግዓዚ ዘማእረር እማሬ፤

ኢትዮጵያ ብክዪ ለውሉዱኪ በመጠነ ራሄል እመ ቆሬ፤

ውሉዱኪ እልፍ ጥብሉላን መዓተ ጸላኢ ጶደሬ፤

መቃብረ እስመ ይወርዱ ለኑባሬ።