ከሚለያዩን ይልቅ የሚያስተባብሩንን ውይይትና ንግግርን የሚያስቀድሙ የአስተዳደር ዘይቤዎችን መፈለግ ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ ነው – ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ

‘It’s The People-To-People Connections That Make A Lasting Impact’: Sahle-Work Zewde, Ethiopia’s first female president & the only serving female head of state in Africa, tells FORBES AFRICA why more leaders should use soft power to achieve shared growth.
መሪዎች ስኬትን ለማምጣት ውይይትና መግባባትን ሊያስቀድሙ ይገባል-ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ
በኢትዮዽያ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንትና ርዕሰ ብሄር ሳህለወርቅ ዘውዴ ከፎርብስ አፍሪካ መጽሄት ጋር በነበራቸው ቆይታ መሪዎች መደበኛ ባልሆነ መንገድ ተንቀሳቅሰው ለጋራ እድገት መስራት እንዳለባቸው አሳሰቡ።
Sahle-Work Zewde has her name etched in political history. A veteran public official having served as an ambassador to Senegal, Djibouti, and France between 1989 and 2006, before her presidency, Zewde was Special Representative to the African Union and Head of the United Nations Office to the African Union. In an email interview, Zwede, who was also on FORBES AFRICA’s list of ‘Africa’s 50 Most Powerful Women’ for its March issue, dwells on why the ‘Africa we want’ will only become a reality with the positive and significant transformation of women’s lives:
በሴኔጋል በጅቡቲ እና ፈረንሳይ የኢትዮዽያ አምባሳደር እንዲሁም የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግስታት ልዩ ተወካይ ሆነው ያገለገሉት ፕሬዝዳንቷ ስማቸው በአፍሪካ ፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ከተካተተ መሰንበቱን በማንሳት ባለፈው መጋቢት ባወጣው ዘገባው ከአፍሪካ 50 ተጽእኖ ፈጣሪ ሴቶች ዝርዝር ውስጥ እንዲካተቱ አድርጓል፡፡
የጾታ መመጣጠንን በሚመለከት በኢትዮዽያ ምን እንደተሰራ በመጽሄቱ ለቀረበላቸው ጥያቄ ፕሬዝዳንቷ እንደገለጹት የእሳቸውና የሌሎች ሴቶች ወደዚህ ስልጣን መምጣት ሃላፊነትና መልካም አጋጣሚ እንዲሁም እርምጃው ለኢትዮዽያም ሆነ ለአፍሪካ ትልቅ እመርታ ነው ብለዋል።
ይሄንን እድል የሚያሰፋና የሚያጠናክሩ እርምጃዎች መወሰድ ካልተቻሉ ሁኔታዎች ወደበፊቱ ሊመለሱ ስለሚችሉ ሁሉም በስራ ላይ ያሉ አመራሮች በተለይም ሴቶቹ በአመራር ስፍራዎች ላይ እያሉ አቅማቸውን ለማሳደግ መጣር አለባቸው ብለዋል፡፡

ለቀጣዮቹ የሴት መሪዎች ዕድሎችን በሚያመቻቹ እንቅስቃሴዎች ላይ መሳተፍ እንዳለባቸውና የተማሩ እና በራስ መተማመን ያላቸው ሴቶችን ማብቃት ላይ መስራት የአሁኖቹ ሴት አመራሮች ሃላፊነትና ግዴታ ስለመሆኑም ተናግረዋል፡፡
የአፍሪካ አገራት ሴቶች በትምህርት ፣ በጤና አገልግሎቶች ፣ በገንዘብ እና በፖለቲካው ዘርፍ ያላቸው ተሳትፎ በማደግ ላይ ቢሆንም በተጨማሪነት መደረግ ያለባቸው በርካታ ነገሮች መኖራቸውን ያነሱት ፕሬዝዳንቷ እንደ አንድ አህጉር እኛ መሪዎች ከንግግር ባለፈ በሁሉም ዘርፍ ለአፍሪካ ሴቶች ተጨባጭ መፍትሄ መስጠት ይኖርብናል ብለዋል ፡፡
የአንድንጅማሮ ግብ ለማሳካት ማንኛውንም መንገድ መጠቀም መልካም ቢሆንም በመግባባት ፣ በመረዳት እና ጤናማ ንግግር በሚኖረው ተጽዕኖ ላይ የተመሠረተ ግንኙነት መፍጠር የተፈለገውን ውጤት ለማግኘት ቀላሉ ዘዴ መሆኑን እንደሚያምኑ ተናግረዋል።አክለውም ፕሬዝዳንቷ ንግግሮችና ውይይቶች ጉልህ ለውጥ እንደሚያመጡ ከ35 አመታት በላይ በሰራ በቆዩባቸው ጊዜያት የተገነዘቡት ነገር መሆኑን አስረድተዋል ።
ለበርካታ አስርት አመታት በዘለቁ የእርስበርስ ጦርነቶች ምክንያት ስትሰቃይ የነበረችው አፍሪካ በተነጻጻሪ አሁን ላይ የተሻለ ምጣኔ ሃብታዊ ለውጦች ማምጣቷን ጠቁመው፤ ከሚለያዩን ይልቅ የሚያስተባብሩንን ውይይትና ንግግርን የሚያስቀድሙ የአስተዳደር ዘይቤዎችን መፈለግ ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ ነው ብለዋል።
እጅጉን በተሳሰረው የዚህ የአለም ስርአት ውስጥ እውነተኛና ዘላቂ ግንኙነት ዘላቂነት እንዲኖራቸው ካስፈለገ የአሁኖቹ መሪዎች ጎታችና ኋላቀር ከሆነው አስተሳሰብና የአመራር ዘይቤ በመፋታት አለማቀፍ አመለካከትን መያዝ የግድ እንደሚላቸው አስረድተዋል።


መረጃ ቲቪን በተሻለ ጥራት እና ፍጥነት እንድናቀርብ እገዛችሁን እንሻለን።
መረጃ ቲቪን ለማገዝ ይህን ሊንክ በመጫን አባል ይህኑ - JOIN Mereja TV