የአንዋር መስጅድ እሳት ቃጠሎ አኩለ ሌሊት ላይ ሲነሳ የፍንዳታ ድምጽ ተሰምቷል።

ተጨማሪ መረጃ አንዋር መስጅድ ቃጠሎ
——————-———————
ሌሊት ረቡዕ ለሐሙስ ሰኔ 20 ቀን 2010 በአንዋር መስጊድ በሴቶች መስጊድ ዙሪያ ሱቆች የተነሳው ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ንጋት ላይ በቁጥጥር ሥር የዋለ ቢሆንም እሳቱ ማለዳ 12:30 ላይም ሙሉሙሉ አልጠፋም፡፡

የተዲፈነ ጭስ ይታያል፡፡ በዙሪያው ሁኔታውን እየተከታተሉ ያሉ የጸጥታ ኀይሎች እንደነገሩኝ መንስኤውን እየመረመሩ ቢሆንም አንድ የዐይን አማኝ ጨምሮ እንደነገረኝ እሳቱ አኩለ ሌሊት ላይ ሲነሳ የፍንዳታ ድምጽ የተሰማ ሲሆን በሌቦች አማካኝነት ከፍተኛ ዝርፊያም ተካሂዷል፡፡

ወጣቶች ባደረጉት ርብርብ የሴቶች መስጊድ መድረሳ ጣሪያ በመነቃቀሉ ምክንያት መስጊዱ ከጥቂት ከቃጠሎ ሊተረፍ ችሏል፡፡ አልሐምዱሊላሂ!
@አቡበክር አለሙ