ቅዱስ ሲኖዶስ: የተዘጉ የቤተ ክርስቲያን በሮች ተከፍተው አገልግሎቱ በፀረ ኮቪድ-19 የጥንቃቄ ተግባራት እየተመራ እንዲፈጸም አዘዘ

ጠቅላይ ቤተ ክህነት ከመንግሥት ጋራ በመነጋገር ትእዛዙን እንዲያስፈጽም መመሪያ ሰጠ፤ አገልግሎቱን በጥንቃቄ ተግባራቱ መሠረት ለማስፈጸም አጥቢያዎች ሓላፊነቱን ይወስዳሉ፤ የሰንበት ት/ቤቶችን በማስተባበር፣ መንፈሳዊ አገልግሎቱ በአግባቡ እንዲከናወን ያደርጋሉ፤ ጥምቀቱ፣ ቊርባኑ፣ ተክሊሉ፣ ፍትሐቱ፥ርቀትን ጠብቆ በተገቢ የልኡካን ቁጥር ይፈጸማል፤ *** የቤተ ክርስቲያን በር በግድ እየተዘጋ በፖሊስ የሚደረገውን ጥበቃ ተቸ፤ ቋሚ ሲኖዶሱ፥ “በስሜ የተደረገ እንጂ የእኔ ውሳኔ አይደለም፤” ሲል አስተባብሏል፤ …