በኤምባሲዎችና በማረሚያ ቤቶች ስር ነቀል የመዋቅር ለውጥ ሊደረግ መሆኑ ታውቋል።

* በኤምባሲዎችና በማረሚያ ቤቶች ስር ነቀል የመዋቅር ለውጥ ሊደረግ መሆኑ ታውቋል።
* ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከዳላሱ ፌስትቫል ከክብር እንግድነት ያገደው * የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ ተደመረ ።
* አሶሳ ሕዝቡ ለጭፍጨፋ የወጡትን ለመከላከል በጋራ ቆሟል።
* የወያኔ ባለስልጣናት መቅበዝበዝ አነጋጋሪ ሆኗል።
* የአሜሪካ መንግስት የኢትዮጵያን መንግስት ለማረጋጋት እየሰራሁ ነው ማለቱ በሕወሓት አባላት ዘንድ ስጋትን ፈጥሯል።
* በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ድፍድፍ ነዳጅ የማምረት ሙከራ ነገ እንደሚጀመር ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስታወቁ።

(ምንሊክ ሳልሳዊ)
የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ አሁን በአገራችን በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የፖለቲካዊ ለውጥ ይደግፋል። በተጨማሪም ድጋፋቸውን የወደፊት ብሩህ ተስፋቸውንና ምኞታቸውን ለጠቅላይ ምኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በነፃነት ለመግለጽ በወጡት ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ላይ በደረሰው ከፍተኛ አደጋ በጣም አዝነናል። ይህን በመልካም የተጀመረውን የሠላም የአንድነትና የፍቅር ጉዞ ለማደፍረስ ታስቦ የተደረገውን አፀያፊ ተግባር አጥብቀን የምናወግዘው መሆናችንን እንገልፃለን። ፈጣሪ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናቱን እንዲሰጣቸው እንለምናለን። ዶክተር አብይ አሕመድ የብዙ አመታት የፍትሕ እና የዴሞክራሲ መስዋትነት ለወቅቱ የላካቸው የለውጥ አቀንቃኝና የኢትዮጵያውያን መቃተት መልስ ናቸው ብሎ ተረድቶታል፥፥ ከ፵ ዓመታት በላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ሲናፍቀው የኖርነውን ኢትዮጵያዊነት አምባገነኖች ሊቀብሩት ከከተቱት ጉድጓድ አውጥተው ስላጎናጸፉን ከልብ የመነጨ ምስጋና እናቀርባለን። የጀመሩትንም የለውጥ ሂደት በእውነተኛ መሰረት ላይ ለመትከል እንዲቻል እኛም ያላሰለሰ ድጋፍ ለመስጠት በምንችለው ለመርዳት ዝግጁ መሆናችንን በዚህ አጋጣሚ መግለጽ እንወዳለን ሲል መግለጫ አውጥቷል።

በአሶሳ በተከሰተው የበርታ ብሔሮች ወረራ ያልተደናገጡ ወጣቶች ተሰባስበው ራሳቸውን በመከላከል በርካ ጉዳት ሊደርስ ከነበረው ግጭት የዳኑ ሲሆን መከላከያ ሰራዊቱም ደርሶ ከበርታዎች ጋር በመታኮስ ከፍተኛ ከሆነ እልቂት ሕዝብ መዳኑን መረጃዎች ተቁመዋል። በሚሊዮን ብሮች ድጋፍ የተቀሰቀሰው ችግር በተደራጁ ራሳቸውን በሚከላከሉ ሀበስሃ ተብለው በሚተሩ ሕዝቡን በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን እንዳያገረሽ ሕዝቡ መዘናጋት የለበትም ተብሏል።

ካለምንም ምክንያት የወያኔ ባለስልጣናትና ካድሬዎቻቸው መቅበዝበዝ አነጋጋሪ ሆኗል። ስልጣናችንን ተነጥቀናል ያሉና ለሃያ ሰባት አመት ሕዝብንና ሃገርን ሲዘርፉና ሲገሉ የኖሩ ባለስልጣናት በዚህ መቀተል እንደማይችሉ ሕዝብ አስረግጦ ከነገራቸው በኋላ በየክልሉ በመዞር ያላቸውን ኔትወርክ ተጠቅመው ከፍተኛ አደጋ በመፍጠር ስራ መጠመዳቸው ታውቋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የአሜሪካ መንግስት የኢትዮጵያን መንግስት ለማረጋጋት እየሰራሁ ነው ማለቱ በሕወሓት አባላት ዘንድ ስጋትን ፈጥሯል። የዘረፍነውንም በሰላም እንዳንበላ ምእራባውያን ከበውናል በማለት የተለያየ ሰበብ በመፍጠር አሜሪካኖችን እየወነጀሉ ይገኛሉ። አሜሪካኖች የገቡበት ሁሉ ሰላም የለም በማለት እየከሰሱ ነው።

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ድፍድፍ ነዳጅ የማምረት ሙከራ ነገ እንደሚጀመር ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስታወቁ። የሚለው አስደሳች ዜና በተሰማ ሰዓታት ውስጥ ሕወሃት በኤምባሲዎችና በማረሚያ ቤቶች የዘረጋው ኔትወርክ ላይ ስር ነቀል የመዋቅር ለውጥ ሊካሔድ መሆኑ ታውቋል። ዝርዝሩ ለጊዜው ቢያዝም በዚህ ጉዳይ ላይ ከፍተኛ የ አሜሪካና የጀርመን አማካሪዎች እየሰሩት መሆኑ ተሰምቷል።

(ምንሊክ ሳልሳዊ)