ባለስልጣናት እግራቸው ላይ ሃውስ አሬስት ብራስሌት (Ankle Monitor) መገጠሙ

* ከባለስልጣናት መሸበርና የኤፍቢአይ የአደባባይ ውሎ እስከ ሻእቢያ ጉያ
* ባለስልጣናት እግራቸው ላይ ሃውስ አሬስት ብራስሌት (Ankle Monitor)  መገጠሙ
* ከደቡብ ሕወሓት የወለዳቸው ቱባ ባለስልጣናት ከድምር መቀነሳቸው
* ኤርትራ ኢትዮጵያና አዲሱ መልካም ዜና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አስመራ በረራ ሊጀምር
* አባይ ጸሓዬ አሶሳን መልቀቁን ተከትሎ የበርታ ብሄር ጦረኞች ከተማውን ማሸበራቸው

*ሁለት መቶ ሃምሳ የሚሆኑ ግለሰቦች ከሃገር እንዳይወጡ ታግደዋል።(Minilik Salsawi)

የደቡብ ክልል ፕሬዝዳንት የሆኑት ደሴ ዳልኬ ስልጣን እንዲለቁ ተጠይቀው አሻፈረኝ ቢሉም ፌዴራል መንግስቱ ዛቻ ስለሰነዘረባቸው ደንብረዋል ፤ የሕወሓትን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማስፈፀምና ኮማንድ ፖስቱን በመምራት ለአስር ሺዎች ሞት እስርና ስደት ተጠያቂ የሆነው ሲራጅ ፈርጌሳ ከስልጣን ቢባረርም ሹመት እንዳይሰጠው ስጋት አሳድሯል። የወላይታ ባለስልጣናት ስልጣን ለቀዋል ቢባልም በሰሩት ወንጀል ተጠይቀው በይቅርታ ወይም በቅጣት ለመለቀቃቸው ምንም መርጃ ሊገኝ ባለመቻሉ የሲዳማ ባለስልጣናት ስልጣን ለመልቀቅ በማገራገር ላይ መሆናቸው ታውቋል። የክልል ባለስልጣናት በከፊል የ አብይ አስተዳደር ድምር መስመር ሊዋጥላቸው ባለመቻሉ እየተሸበሩ ነው፤ ሕዝብን አሸባሪ ብለው ሲፈርጁ የኖሩት ባለስልታናት በራሳቸው ስብር እየተናጡ ነው።

የ አሜሪካ የምርመራ ተቋም የህወሃትን ሰዎችና ካድሬዎቻቸውን ማሸበሩን የቀጠለ ሲሆን የሕወሓት አመራሮች በካድሬዎቻቸው በኩል የተለያዩ ጽሁፎችን በመልቀቅ መረጋጋታቸውን እንደተሰረቁ በማሳበቅ ላይ ይገኛሉ። ወንጀለኛው ተለይቶ ባልታወቀበት በዚህ ወቅት ላይ ሕወሓቶች መረጋጋት ሲኖርባቸው ወሬያቸው ሁሉ ቦምብና ፍንዳታ መሆኑ ግርምትን ፈጥሯል። መርማሪዎቹ ምርመራቸው ሻእቢያ ጉያ ድረስ መሆኑ ደግሞ ሌላ ግርምትን የፈጠረ መረጃ ተገኝቷል። መርማሪዎቹ መስቀር አደባባይን መበርበራቸውን ቀጥለዋል።

ሌላ የመርማሪዎች አከባቢ የተገኘ ዜና ለከፍተኛ የደሕንነት ባለስልጣናትና ለተወሰኑ የሕወሃት ጄኔራሎች ሃውስ አሬስት ብራስሌት (Ankle Monitor) ተብሎ የሚጠራው የፖሊሶች የመከታተያ ማሽን እግራቸው ላይ መገጠሙ ነው። ይህ ማሽን ስራው ባለስልጣናቱ በሚንቀሳቀሱበት ሁሉ ክትትል ማድረግ መሆኑ ታውቋል። ለኢትዮጵያ አየር መንገድ በተላለፈው የስም ዝርዝር መሰረት ቁጥራቸው ሁለት መቶ ሃምሳ የሚሆኑ ግለሰቦች ከሃገር እንዳይወጡ ታግደዋል። እንዲሁም አሜሪካ በመንግስት ተቋማት ላይ ከፍተኛ ክትትል እንዲደረግ ማሳሰቧን ተከትሎ አሜሪካን አገር በሰለጠኑ የደሕንነት ሰዎች ስራዎች መጀመራቸው ታውቋል።

የኤርትራ ባለስልጣናት ጉብኝትን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አስመራ በረራ ሊጀምር መሆኑ ታውቋል በዚህም መሰረት የመጀመሪያው በረራ ለኢትዮጵያውያን አዲስ አመት ሊሆን ይችላል የሚል መረጃ ተገኝቷል ይህ በረራ አርቲስቶችን ይዞ አስመራን በፌስትቫል ያናውጣታል ተብሏል። በሁለቱ ሕዝቦች ላይ አዲሱ የፍቅር የሰላምና የእርቅ ግንኙነት ደስታን ፈጥሯል።

በ አሶሳ ያለው ጉዳይ በጣም አደገኛ መሆኑ ታውቋል። የበርታ ብሔር አባላት የኦሮሞና የ አማራ ብሄሮችን ለማጥቃት መሳሪያዎቻቸውን ይዘው አሶሳን እያሸበሯት ነው፣ ባለፈው ሳምንት የሕወሓት አመራር የሆነው አባይ ጸሐዬ አሶሳ ከርሞ ከተመለሰ በኋላ አሶሳ ሰላሟን አጥታለች በብሔር ግጭት እየታመሰች መሆኑ ታውቋል። #MinilikSalsawi