አሜሪካ የቅዳሜውን ጥቃት ለማጣራት የሚያግዙ የኤፍ ቢ አይ ባለሙያዎችን ትልካለች

አሜሪካ የቅዳሜውን ጥቃት ለማጣራት የሚያግዙ የኤፍ ቢ አይ ባለሙያዎችን ትልካለች

(ኤፍ ቢ ሲ)  አሜሪካ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን በመደገፍ በተካሄደው ሰልፍ ላይ የተፈፀመው ጥቃት አቀናባሪዎች ላይ የተጀመረውን ምርመራ የኤፍ ቢ አይ ባለሙያዎችን በመላክ ድጋፍ እንደምታደርግ አስታወቀች።

የሃገሪቱ ምክትል የንግድ ሚኒስትር ጊልበርት ካፕላን ዛሬ ከኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ጋር ተወያይተዋል።

በዚህ ወቅትም ሃገራቸው የቅዳሜውን ጥቃት አቀናባሪዎች ለማጣራት በሚደረገው ሂደት በምርመራ ባለሙያዎቿ አማካኝነት ድጋፍ እንደምታደርግ ተናግረዋል።

ምክትል የንግድ ሚኒስትሩ የአሜሪካ የፌደራል የምርመራ ቢሮ (ኤፍ ቢ አይ) ባለሙያዎች የጥቃቱን ፈጻሚዎችና ጉዳዩን ለማጣራት በሚደረገው ሂደት ይሳተፋሉ ብለዋል።

በውይይታቸው ወቅት በቅዳሜው የድጋፍ ሰልፍ በተፈጸመው ጥቃት ሳቢያ በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሃዘንም፥ በራሳቸውና በአሜሪካ መንግስት ስም ገልጸዋል።

በጥቃቱ ሳቢያ ሰለባ ለሆኑ ቤተሰቦችም መጽናናትን ተመኝተዋል።