የአዲስ አበባው ሰልፍ ዝግጅት

ነገ አዲስ አበባ በአይነቱ ለየት ያለ ሕዝባዊ ሰልፍ ታስተናግዳለች። መስቀል አደባባይ እስከዛሬ ያስተናገደው የሰልፍ አይነት አንድም በመንግሥት ተቀስቅሶ ለድጋፍ የወጣ ሰልፈኛ አንድም አሁን ተፎካካሪ በሚል ስያሜያቸው በተቀየረላቸው የተቃውሞ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጥሪ በመንግሥት ይፈጸማል የሚለውን ለመቃወም የወጣ ተሰላፊን ነበር።…