ኢትዮጵያ ከአንድ ሚሊየን ህዝቧ ውስጥ ለ16 ሰዎች ብቻ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ እያደረገች መሆኑ ተገለጸ።

ኢትዮጵያ ከአንድ ሚሊየን ህዝቧ ውስጥ ለ16 ሰዎች ብቻ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ እያደረገች መሆኑ ተገለጸ።
ወርልዶ ሜትር (Worldo meter) እንደተባለው ድረ ገፅ ከሆነ፤ ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ምርመራን በማድረግ ከ50 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ካላቸው የአለም ሀገራት የመጨረሻ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
በኢትዮጵያ የሚመረመረው ህዝብ ቁጥር ያነሰበት ምክንያት ምልክቱ የታየባቸውና በቫይረሱ ተጠቂ ከሆኑ ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸው ሰዎች ብቻ የሚመረመሩ በመሆኑ ሲሆን ትናንት የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በስራ ባህሪያቸው ለቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች ላይ የሚደረገው ምርመራ በተለይም ቫይረሱ በተገኘባቸው አካባቢዎች ላይ ምርመራው በስፋት እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።
እስካሁን በኢትዮጵያ ለ1ሺ 843 ያህል ሰውዎች ብቻም ምርመራ መደረጉን የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መረጃ ያስረዳል።
የኮሮና ምርመራን ለህዝባቸው በማድረስ ከኢትዮጵያ ቀጥሎ የከፋ አፈፃፀም ያሳዩት ባንግላዴሽና ናይጄርያ ናቸው፡፡
ባንግላዴሽ ከ 1 ሚሊዮኑ 18 ሰው እየተመረመረ ሲሆን ናይጀርያ ደግሞ 19 ነው እያስመረመረች ያለችው፡፡
ደቡብ ኮርያ በብዛት ምርመራውን በማድረግ በአንደኝነት ስትቀመጥ ከአንድ ሚሊዮን ህዝብ ውስጥ 8 ሺህ 9 መቶ 96 ምርመራውን ያገኛል፡፡
ሲንጋፖር ከ 1 ሚሊዮን ህዝብ ውስጥ 6 ሺህ 6 መቶ 66 በማስመርመር ሁለተኛ ፤ ማሌዢያ ደግሞ ከ 1 ሚሊዮን ህዝብ ውስጥ 1 ሺህ 6 መቶ 5 በማስመርመር ሶስተኛ ሆነዋል፡፡
በእንግሊዝ መንግስት በቀን ከ 100 ሺህ ሰው በላይ ማስመርመር እንደማይችል ለህዝቡ በመግለፁ ከፍተኛ ቁጣን አስተናግዷል፡፡
Ethio FM