መስቀል አደባባይ ለህዝባዊ አደባባይነት በሚመጥን መልኩ በዘመናዊ መልኩ ሊገነባ ነው ተባለ

መስቀል አደባባይ ለህዝባዊ አደባባይነት በሚመጥን መልኩ ከመሬት በታች እስከ 1400 ተሽከርካሪ ለማቆም የሚያስችል የመኪና ማቆሚያ በዘመናዊ መልኩ ይገነባል
መስቀል አደባባይ ለህዝባዊ አደባባይነት በሚመጥን መልኩ ከመሬት በታች እስከ 1400 ተሽከርካሪ ለማቆም የሚያስችል የመኪና ማቆሚያ በዘመናዊ መልኩ ይገነባል።የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ ከመስቀል አደባባይ ማዘጋጃ ቤት ደረስ የሚካሄደው መልሶ ማልማትና የአረንጓዴ ስፍራ ግንባታ ቅድመ ዝግጅት ያለበትን ደረጃ ተመልክተዋል።
ለመልሶ ማልማቱና አረንጓዴ ስፍራ የቦታ ዝግጅትና የወሰን ማስከበር ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማና የአዲስ አበባ የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ በጋራ ዝግጅቱን ተመልክተዋል።በመስቀል አደባባይ መልሶ ግንባታ ቦታው ለህዝባዊ አደባባይነት በሚመጥን መልኩ በዘመናዊ መልኩ የሚገነባ ይሆናል።
ቦታው ላይ ከመሬት በታች እስከ 1400 ተሽከርካሪ ለማቆም የሚያስችል የመኪና ማቆሚያ ይገነባል።ፋውንቴንና የተለያዩ መዝናኛዎችን ባካተተ መልኩ የሚገነባው መስቀል አደባባይ መልሶ ግንባታው በለግሀር— ቸርችል አደባባይ እስከ ፒያሳ ድረስ በሚሰራው አረንጓዴ ስፍራ ፕሮጀክት ጋር የተያያዘ ነው።
ከመስቀል አደባባይ እስከ ፒያሳ ድረስ ያለው መንገድ ትይዩ በሆነ መልኩ የሚገነባ ሲሆን በመንገዶቹ ጠርዝ ያለው የእግረኞች መሄጃ ሰፋ ባለ መልኩ የሚገነባ ሲሆን ለአካል ጉዳተኞች እንዲመች ተደርጎ እንዲሁም የብስክሌት መጓጓዧን ባካተተ መልኩ ይገነባል።ፕሮጀክቱ ዲዛይኑ የተጠናቀቀ ሲሆን በቅርብ ወደ ስራ ይገባል።በቀጣይም ይህን እንደመነሻ በመውሰድ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ተመሳሳይ የማስዋብ ስራዎች የሚተገበሩ ይሆናል።