ሰለ ኮሮና ቫይረስ የሚነሱ ጥያቄዎችና ሳይንሳዊ መልሶቻቸው

DW : ኮቪድ-19 ኮሮና ቫየረሰ በቻይና ከተከሰተ ከጎርጎሪያኑ ታሀሳስ መጨረሻ ጀምሮ ቫየረሱ ከየት መጣ? ገዳይነቱስ ምን ያህል ነዉ? በግዑዝ ነገሮች ላይስ ምን ያህል ጊዜ ይቆያል?የሚሉትና ሌሎቸ አነዚህን የመሳሰሉ ጥያቄዎች ለወራት በብዙዎች ዘንድ ተደጋግመው የተነሱ   ጉዳዮች ናቸዉ ፡፡ከዚህ ቀደም ተከስቶ የነበረዉና ኖቨል ኮሮና ቫይረስን ባስከተለዉ  ሳረስ/ SARS-CoV-2/ ላይም ከኮሮና ቫይረስ ጋር ያለዉ ዝምድና ምንድን ነዉ? በሚል አሁንም ድረስ  የሚነሳ ጥያቄም አለ ፡፡
ጥያቄዎቹ በፌስቡክ ፤በቲዊተርና ጎግልን በመሳሰሉ የመረጃ ቋቶች ተደጋግመው የተነሱ ሲሆን፤ ተመራማሪዎችም በተቻለ መጠንና ፍጥነት  መርምሮችን በማድረግ አነዚህና ሌሎች ጥያቄዎችን ለመመለስ እየሞከሩ ነው  ፡፡ እስካሁን የተደረሱባቸዉን ግኝቶች እነሆ ፡፡
ኮቪድ 19 ክሳርስ  ጋር ተመሳሳይ ነውን ?
በጎርጎሪያኑ ዘመን አቆጣጠር በ2003 ተከስቶ የነበረው የሳርስ ቫይረስ ፤  ኮቪድ 19ኝን ከሚያመጡት ቫይረሶች ጋር እጅግ ተቀራራቢ ቢሆኑም በሽታዎቹ ግን የተለያዩ ናቸዉ፡፡የሳርስ በሽታ የመዛመት አቅሙ አነስተኛ የነበረ ቢሆንም የመግደል አቅሙ ግን 9 .6 በመቶና  እጅግ ከፍተኛ የሚባል ነበር፡፡ ኮቪድ -19 በአንፃሩ የመሰራጨት አቅሙ እጅግ ከፍተኛ ሲሆን የመግደል አቅሙ 2 በመቶ ሆኖ  ከእለት ወደ ዕለት እየጨመረ የመጣ በሽታ ነው፡፡ሁለቱም ግን ከእንስሳት  ወደ ሰው የተላለፉ ናቸዉ፡፡

Coronavirus- COVID-19 - Mikrografie (picture-alliance/CDC) ሌላዉ ቫይረሱ ከእንሥሳት የመጣ ነዉን?
ቫይረሱ ከእንሥሳት የመጣ ነዉን?የሚለዉ ሌላዉ ጥያቄ ሲሆን
በእርግጥ የኮሮና ቫይረስ ከአንስሳት በተለይም ከሌሊት ወፎች ወደ ሰው የተላለፈ በሽታ ነው ተበሎ በንድፈ-ሀሳብ ደረጃ በሰፊዉ ይታመናል፡፡ነገር ግን ቫይረሱ በእንስሳቱ ውስጥ በነበረበት ጊዜ የሰው ልጆችን ለማጥቃትና በሰዉነት ውስጥ ለመባዛት የሚያስቸለዉን ተከታታይና ከፍተኛ የዘር-መል ሂደቶችን ማለፉን ተመራማሪዎች ይገልጻሉ፡፡ ነገር ግን ቫይረሱ ሰዎችን ከማጥቃቱ በፊት ከአንስሳት ወደ  አንስሳት ስለመተላለፉ አስካሁን ድረስ ሳይንሳዊ በሆነ ንድፈ-ሀሳብ  አልተረጋገጠም፡፡
ኔቸር  የተባለዉ መጽሄት ባለፈው የካቲት ወር መጀመሪያ ባወጣዉ እትም  ኖቭል ኮሮና ቫይረስ  በዘረ-መል ደረጃ 96 በመቶ  ከሌሊት ወፍ ኮሮና ቫይረስ  ጋር ተመሳሳይነት  አንዳለዉ የሚያሳይ ጥናት ይዞ ወጥቶ ነበር ፡፡ አንዳንድ የሴራ  ንድፈ ሀሳብ አራማጆች  በበኩላቸው  ቫይረሱ ሰው ሰራሽ የላብራቶሪ ውጤት ነው ብለው ይከራከራሉ ፡፡ያም ሆኖ በማዕከላዊ ቻይና  የሁቤይ  ግዛት  መዲና  በሆነችው ዉሃን ከተማ ሳርስ ኮቪ 2  ለመጀመሪያ ጊዜ ከእንስሳት ወደ ሰው መተላለፉን የሚያሳይ ጠንካራ ማስረጃ አለ ፡፡
የኮቪድ 19 በሽታ ምልክት ለማሳየት ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል?
የአንድ በሽታ የመራቢያ ጊዜ በ እንገሊዘኛ አጠራሩ ኢንኪዩቤሽን ፔሬድ (incubation period)  በሽታ አምጪ ተዋህሲያን  ወደ ሰውነት ከገቡበት  አንስቶ የበሽታው ምልክት እስከሚታይበት ድረስ ያለው ጊዜ ነው፡፡
ምልክቶቹ በምን ያህል ቀን ሊታይበት ይችላል የሚለው  በግለሰቡ የበሽታ መከላከል አቅም  የሚወሰን ቢሆንም  አንድ ሰው የበሽታው አማጭ ቫይረስ ወደ ሰውነቱ ከገባበት ከመጀመሪያው እለት አንስቶ እስከ አስራ አራተኛው ቀን ድረስ የበሽታውን ምልክቶች ሊያሳይ ይችላል፡፡ በአብዛኛው ግን እነዚህ ምልክቶች አንድ ሰው በቫይረሱ በተያዘ በአምስተኛው ቀን አከባቢ ሊታዩ እንደሚችሉም የኮቪድ 19ን  የመራቢያ ጊዜ በተመለከተ የተደረጉ  ጥናቶች ያሳያሉ፡፡
የኮቪድ-19 ምልክቶች ምንምን ናቸው?
በቫይረሱ የተያዘ ሰው በመጀመሪያ ትኩሳት ደረቅ ሳል  የድካም ስሜት  ከዚያም የጉሮሮ መድረቅ፣ መቁሰል፣ መከርከርና ለመተንፈሰ መቸገር  /የትንፋሽ መቆራረጥ/ ያስከትላል፡፡ከዚሀ በተጨማሪ በአንዳንድ ታማሚዎች ላይ  የመገጣጠሚያ ሀመም፤ የአፍንጫ መታፈን፤ የተቅማጥና የማቀለሽለሽ ምልክት ሊታዩባቸው ይችላል፡፡
እነዚህ የበሽታ ምልክቶች ሲጀምሩ ቀለል ባለ መለክ ጀምረው ቀስ በቀስ ግን እየጨመሩ የሚሄዱ ናቸው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ደግሞ በበሽታው ተይዘውም ምንም ዓይነት ምልክትም ይሁን ህመም ላይታይባቸው ይችላል፡፡ነገር ግን ወደ ሌላ ሰው ሊያሰራጩ ይችላሉ፡፡በኮቪድ 19 ከተያዙ ከስድስት ሰዎች በአንዱ  በከፍተኛ ሁኔታ መታመም እና የመተንፈስ ችግር ሊያጋጥም ይችላል ፡፡በተለይ እድሜያቸው የገፉ እና ከዚህ ቀደም ሌሎች በሽታዎች ያሉባቸዉ ከሆነ፡፡
የቫይረሱ የመግደል እቅም ምን ያህል ነው ?
የኮሮና ቫየረስ ይገድላል ወይ? የሚለዉ ጠያቄ ተደጋግሞ የሚነሳ ጠያቄ ነዉ ፡፡ነገር ግን መልሱ  “አወ” ወይም “አይደለም” በሚል በቀላሉ የሚመለስ አይደለም ልክ የጉንፋንና የመኪና አደጋን ሞት በትክክል መተነበይ አንደማይችለው ሁሉ  መናገር የሚቻለው ለሞት ሊያበቁ ይችሉ ይሆናል ተብለው የሚጠቀሱ ምናልባታዊ መረጃዎችን ነዉ. ያም ቢሆን የኮቪድ-19 ጉዳይ ቀላል አይደለም፡፡  አናም የቁጥሮችን እና የቃላት አጠቃቀምን ትርጉም ያለው ለማድረግና ኮሮናን በተመለከት ያለውን ግራ መጋባት ለማስወገድ አሃዛዊ ትንታኔ ማድረግን ይጠይቃል፡፡
ክለንደኑ የንጽህና እና ትሮፒካል  ህከመና ትምህርት ቤት የሂሳብ ሊቀ  የሆኑት አዳም ኩቻርስኪ የቫይረሱ የሞት  መጠን ከ 0.5 እስከ 2% እንደሆነ ያሰላሉ ፡፡ ያ ማለት በቫይረሱ ከተጠቁ  አንድ መቶ ሰዎች መካከል አንድ ወይም ሁለት ሰዎች ይሞታሉ ማለት ነው፡፡
ቫይረሱ በአየር ውስጥ ወይም በሌሎች ቁሶች ላይ ለምን ያህል ጊዜ ሊቆይ ይችላል?
የኮሮና ቫየርስ የመተንፈሻ አካላትን የሚያጠቃ በሽታ በመሆኑ ቫይረሱ በዋነኝነት የሚተላለፈው በቫየረሱ የተጠቃ ሰው በሚስልበተ ወይም በሚያስነጥስበት ጊዜ ወደ አየር በሚለቀቁ ጠብታዎች ነው፡፡
አንደ የጀርመን የፌደራል የስጋት ምዘና ተቋም  (ቢኤፍ አር)  የመጀመሪያዎቹ የላቦራቶሪ ሙከራዎች እንደሚያመለክቱት  ከኮቪደ-19 በፊት ተከስቶ በነበረው በኖብል ሳረስ ኮቪ-2/ SARS-CoV-2/ በጣም በተበከለ  በአየር  ለሦስት ሰዓታት ያህል  በመዳብነከ ቁሶቸ እስከ አራት ሰአታት በካርቶን እስከ 24 ሰዓታት እና በማይዝግ ብረት እና በፕላስቲክ ደገሞ ከሁለት ወይም ሶስት ቀናት የቆያል ፡፡
ግን መልካሙ ዜና ቫይረሱ ከሰዎች ሰውነት ከወጣ በሕይወት ለመኖር ቀጠተኛ የሆነ አስቻይ ሁኔታ እንዲኖር ይፈልጋል፡፡ ያ ከሌለ ቫይረሱ እራሱን ማባዛትና ማቆየት ስለማይችል  በጠቂት ጊዜ ይሞታል ፡፡በሌላ በኩል  በቁሶች ላይ የተወሰን ጊዜ በህይወት የመቆየት እድል ቢኖረዉ እንኳ በዚሀ ሁኔታ ሰዎችን የማጥቃት  እድሉ ደካማ መሆኑን ተመራማሪዎች ይገልፃሉ፡፡
በተጨማሪም ከላይ የተጠቀሰው  የቫይረሱ በህይወት የመቆየት እድል  በተመቻቸ የቤተ-ሙከራ ሁኔታ የተጠና ሲሆን የሙቀትና የቀዘቃዜ ለውጥ እንዲሁም የፀሐይ ብርሀንን የመሳሰሉ ውጫዊ ምክንያቶች ቫይረሱ በቁሶች ላይ ተረጋገቶ እንዳይቀመጥ ተፅኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ ፡፡
ራስን ከቫይረሱ እንዴት መጠበቅ ይቻላል?
ኮቪድ 19  ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላው ዓለም በሚገኙ 187 የተሰራጨ ሲሆን በዚህም ሳቢያ እስካሁን 4 መቶ  ሺህ የሚጠጉ  ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡ ከ 17 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ለሀልፈተ ህይዎት ተዳረገዋል ።በመሆኑም ራሰን ከዚህ ወረርሽኝ ለመጠበቅ የበሽታዉ መልክቶች ካባቸዉ ሰዎች መራቅ፣  ቢሚያስነጥሱና በሚያሰሉበት ወቀት ተገቢዉን ጥንቃቄ ማደረግ ፣ እጅን እዘዉትሮ መታጠብ ፣ ከሌሎች ሰዎች አካላዊ ርቀትን መጠበቅና እና ክማሕህበራዊ ግንኙነቶች ለጊዜው መራቅ ያስፈልጋል። እነዚህንና የመሳሰሉትን ጥንቃቄዎች  በማድረግ  እራስን ለመጠበቅ ብቻ ሳይሆን የቫይረሱን ስርጭትም ለመግታት የሚረዳ ነው።ያ ካልሆነ ግን የቫይረሱ ሰርጭት ጠንካራ የጤና ሰረአት የዘርጉትን ጀርመንን የመሳሰሉ ሀገሮች ሳይቀር የሚያሽመደምድ መሆኑን ባለሙያዎች እያስጠንቀቁ ነዉ። ለዚሀም የመሰላል በጀርመን የፌደራል የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ኤጀንሲ ሮበርት ኮህ የተባለዉ ተቋም  ፕሬዝዳንት  ሎተር ዊለር የጥንቃቄ እርምጃዎቹ ያለመታከት መተግበር  አለባቸው ሲሉ አፅናኦት የሰጡት፡፡ ያካለሆን ግን ፣ በመጪዎቹ በሁለት ወይም በሦስት ወራት ውስጥ  በጀርመን ሀገር ብቻ 10 ሚሊዮን ተጨማሪ የቫይረሱ ተጠቂዎች ሊኖሩ ይችላሉ በማለት አስጠንቅቀዋል፡፡
Coronavirus in Russland St. Petersburg Testlabor (picture-alliance/dpa/Sputnik/A. Danichev) አስካሁን ክትባት ወይም መድሃኒት አልተገኘምን?
በመሰረቱ ውጤታማ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ክትባት ለማዘጋጀት በተለምዶ ዓመታትን ይወስዳል። ያም ሆኖ  በአለም ዙሪያ በኮሮና ቫይረስ ክትባት ላይ ያተኮሩ 47 በሂደት ላይ ያሉ ምርምሮች መኖራቸዉን የጀርመኑ የመድሃኒት አምራች ኩባንያዎች ማህበር መረጃ ያሳያል ፡፡ ከነዚህም ውስጥ አነዱና ዋነኛው የጀርመኑ ኪዩር ቫክ የተሰኘዉ ኩባንያ ሲሆን፣የጀርመኑ የተላላፊ በሽታዎች ምርምር ማዕከልም (DZIF)  ቫይረሱን መቋቋም የሚያሰችል ክትባት ለማግኘት ምርምር በማድረግ ላይ ያለ ተቋም ነው ፡፡ የተቋሙ ተመራማሪዎች ቀደም ሲል የተዘጋጁና ጥቅም ላይ የዋሉ  ክትባቶችን እንደመነሻ በመጠቀም  የኮሮቫይረስን ክትባት ለማገኘት እየሰሩ ነው ።
ምንም እንኳን  ሊቃውንቱ በከፍተኛ  ደረጃ  እየሠሩ ቢሆንም በዚህ አመት ገበያ ላይ የሚውል መደበኛ ክትባት መጀመር አዳጋች የመሰላል፡፡ መክንያቱም ከትባቱን ለማረጋገጥ የሚረዱ  ወሳኝ የሚባሉትን ክሊኒካዊ የምርምር ሂደቶች ለማለፍ ረዘም ያለ ጊዜ ይጠይቃልና፡፡ ነገር ግን ክዚህ ምርምር ጎን ለጎን  “ፓሲቭ ኢሚዩናየዜሽን”የተባለ በጊዜያዊነት ቫየረሱን ለመቋቋም የሚያስችል ከትባት በመፍጠር ላይ ናችው፡፡ከትባቱ ከዚሀ ቀደም ከበሽታዉ ካገገሙ ሰዎች  ደም ውስጥ የተገኘውን ለየት ያለ ተሐዋሲውን የመቋቋም  የተፈጥሮ ነጥረ-ነገር  በመጠቀም በክትባት መልክ የሚሰጥና ቫይረሱን ለመዋጋት የሚያስችል  ነው።

ይህ ክትባት ፤ የታማሚው ሰውነት በራሱ የበሽታ መከላከያ ስላላመረተ የሚሰጥ ድጋፍ  ሲሆን  የራሱ የሆነ ጥቅም እና ጉዳት አለው።  ጥቅሙ ቫይረሱን ለመዋጋትና በሽታውን ለመከላከል ማስቻሉ ሲሆን ጉዳቱ ደግሞ እርዳታው  ዘላቂ አለመሆኑና ለአጭር ጊዜ ብቻ የሚያገለግል መሆኑ ነው። ኮቪድ 19ኝን የሚፈውስ መድሃኒትና የሚከላከል ክትባት ለማግኘት የሚደረገው ምርምር  በዚህ መልኩ የቀጠል ሲሆን
ለጊዜዉ ያለዉ በቸኛ መፍትሄ ግን ራሰን ከቫይረሱ መጠበቅ ብቻ ነዉ። ኮቪድ 19 በሽታ በቫይረስ አማካይነት የሚከሰት በሽታ በመሆኑም ፀረ- ባክቴሪያ መድሃኒቶች  የኮቪድ 19 በሽታ ለመዳን አይረዱም፡የህመም ማሰታገሻዎችም የሚመከሩ አይደሉም።
በአሁኑ ወቅት የኮሮና በሽታን ለመከላከል የሚረዳ መደሃኒት ለማገኘት በዓለም ዙሪያ ወደ 70 የሚጠጉ መድኃኒቶች ላይ ሙከራ እየተካሄደ ነው፡፡ክጀርመን የመድኃኒት ቁጥጥር ኮሚሽን ሊቀመንበርና ለሀከመና ባለሙያዉ  ወልፍ-ዲተር ሉድቪሽ ከነዚሀ መካከል ሁለቱ የተሻሉ ናቸው ።
“ሪሜዲቪር እና ሃይድሮክሎሎሮኪን በእርግጠኝነት የምስማማባቸውና በገልፅ በአንደኛ እና በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚቀመጡ ናቸው ፡፡ ምክንያቱም መድሀኒቶቹ የበለጠ ተስማሚና በአሁኑ ጊዜ ከሌሎች መድኃኒቶች ጋር ያላቸው መስተጋብርም አነስተኛ ነው፡፡ ለመድሃኒት ቤቶችም  ምን ያህል ክሎሮኪን ወይም ሃይድሮክሎክሎኪን እንዳላቸው ጥያቄዉ ቀደም በሎ ቀርቧል ።”

 

ሚድቪር ኢቦላን ለማከም ጥቅም ላይ የዋለ መድሀኒት ሲሆን በአሁኑ ወቀት በጀርመን ዱሰልዶርፍ ከተማ በሚገኝ ዩንቭርሲቲ ከሊኒክ  ሁለት በጠና በታመሙ የቫየረሱ ተጠቂዎች ለማከም እየተሞከር ነው፡፡ ከሊኒኩ በዚህ ሙከራ ላይ ስለተገኘው ዉጤት እስካሁን ያለው ነገር የለም፡፡
በሁለተኛ ደረጃ በሙከራ ላይ ያለው መድሃኒት ደገሞ ፣ ክሎሮኪን የተባለዉ የወባ መድሀኒት ነዉ፡፡
”  የወባ መድሃኒት በእኛ ዘንድ በጣም የታወቀ ነው። ይህ ነጥረ-ነገር ለብዙ ዓመታት በፀረ-ቫይረስ ዉህድነቱ  የታወቀ ሲሆን  የሕዋስ ጥናቶች  እነደሚያሳዩት ክሎሮኩዊን እና ሃይድሮክሎሮኪን ሁለቱም የሳርስ ቫይረሶችን ለመዋጋት ችለዋል፡፡ ይህ መድሃኒት በእርግጠኝነት አስደናቂ ነው፡፡ ምክንያቱም  በሌሎች ምልከታዎች የተረጋገጠ ሆኖ በመገኘቱ  በከፍተኛ ደረጃ  በCOVID-19  ለተጠቁ ሰዎች   አማራጭ ሕከምና ሊሆን ይችላል ፡፡”
ከእነዚህ ዉህዶች መካከል አንዱ ታማሚዎችን የሚረዳ መሆኑ ከተረጋገጠና የመደሃኒተ ቁጥጥር ባለሰለጣናት  ፈጣን መላሽ ከሰጡ ሉዲቪሽ ኧነደሚሉት በተያዘዉ አመት በአዉሮፓ በቫይረሱ ተጥቀተዉ በሳንባ ምች ለሚሰቃዩ ሰዎች መፍትሄ ሊገኝ ይችላል ፡፡ነገር ግን እስካሁን የተረጋገጠ ነገር የለም፡፡ በብዙ የመደሃኒት አምራች ኩባንያዎችም ሁኔታውን ገንዘብ የማግኛ ዘዴ የማድረግ አዝማሚያ ይታያል፡፡ እንዲህ መሰሎቹ ምርመሮች ግን እጅግ ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸው መሆኑን ወልፍ-ዲተር ሉድቪሽ ያስጠነቅቃሉ፡፡

“.በአስቸኳይ የህከምና መድሃኒቶች  ፍላጎትና አማራጮችን ሰበብ በማደረግ በእርግጥ ብዙ ገንዘብ ማግኘት ይችላል፡፡ ስለዚህ ለነፃ ሳይንቲስቶች እና ክሊኒኮች እነዚህን ጥናቶችና ውጤቶቻቸውን በጣም በጥንቃቄ መመርመር እና የመረጃ እሴታቸውን መመዘን እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው ፡፡”፡፡
የኮሮና ቫይረስ ክቤተ እንስሳት ወደ ሰው ሊተላለፍ ይችላላን?
መለሱ አወ ይተላለፋል የሚልሲሆን ፤ በዚህ የተነሳ የስዊስ ፌዴራል የምግብ ደህንነት እና የእንስሳት ጤና ጥበቃ ጽ / ቤትም (BLV) የቤት እንስሳት ያሏቸዉ ሰዎች ከእንስሳቱ ጋር ንክኪ እንዳይኖራቸው ይመክራል ፡፡ ነገር ግን  ዉሻና ድመትን የመሳሰሉ የቤት እንስሣት  እስካሁን ምንም አይነት የመጠቃት ወይም የህመም ምልክቶች  አልታየባችዉም፡፡ይህ ሁኔታ አደጋውን ለመገመት  ከባድ ቢያደርገዉም ፤ እንስሳቱ  በበሽታው ክተያዙ በንድፈ ሃሳቡ ደረጃ ቫይረሱን ሊያሰራጩ ይችላሉ ፡፡ለምሳሌ ሳርስ የተባለውን በሽታ የሚያሰከትለው የኮሮና ቫይረስ ከእንሥሳት ወደ ሰው የተላለፈ እንደነበር ልብ ይሏል፡፡
ነብሰ ጡር ሴቶችሰ የበለጠ ተጋላጭ ናቸውን?
የኮሮና ወረርኝ  እድሜያቸው የገፋ ሰዎች፤ እነዲሁም በከቪድ 19 ከመያዛቸው በፊት እንደ ከፍተኛ የደም ግፊት፤ የልብ ድካም፤ ስኳር እንዲሁም የአስም እና የሳንባ ካንሰር ያለባቸውን ሰዎች በይበልጥ እያጠቃ ይገኛል፡፡ ዓለም ቀፉ የጤና ድርጅት እና የጀርመን የፌደራል የጤና ትምህርት ማዕከል  መረጃ መሠረት ነብሰጡር ሴቶች በበሽታው ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ ነዉ ከሚባሉት  ዝርዝር ውስጥ አልተካተቱም ፡፡ ሆኖም ፣ ነፍሰ ጡር ሴቶች አርግዝናው በሰዉነታቸው ላይ ከሚያሳድረዉ ጫና አንጻር ልዩ ጥንቃቄ አንዲያደርጉ  ይመከራል፡፡
ተመራማሪዎች እስካሁን ባገኙት ጥናት መሰረት ልጆች በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ለከባድ በሽታ የመጋለጥ አድላችው አነስተኛ ነው ፡ በዚህ የተነሳ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ልጆች ብዙውን ጊዜ በሽታው በመካከለኛ ደረጃ ነዉ ሊያጠቃቸው የሚችለው ፡፡ያ ማለት ግን አስካሁን በቫይረሱ የሞቱ የሉም ማለት አይደለም፡የአለም አቀፉ የጤና ድርጅት ዘገባ አነደሚያሳየዉ ፡የበሽታው ስርጭት  በማንኛውም የእድሜ ክልል ሕጻናትን እና ወጣቶችን ሳይቀር እያጠቃ  ነው ፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ቫይረሱ አዲስ  በተወለዱ ሕፃናት ላይ መታየቱንም የሚያሳዩ ዘገባዎች አሉ፡፡ሆኖም ግን  ቫይረሱ የተላለፈው በእርግዝና ወቅት ይሁን በወሊድ ጊዜ ወይም ከወሊድ በኋላ የሚለው በውል አይታወቅም ፡፡
ሰለሆነም ወረሽኙ ደረጃው ቢለያይም ሁሉንም የሕበረተሰብ ክፍል የሚያጠቃ በመሆኑ ሁሉም ሰው በሽታውን ለመከላከል የሚያስችሉ ጥንቃቄዎችን ማድረግ አለበት፡፡