" /> የኮሮና ቫይረስ የመዳን ሁኔታው ከፍተኛ በመሆኑ መፍራትና መደናገጥ ሳይሆን ላለመያዝ መጠንቀቅ አስፈላጊ ነው ተባለ | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

የኮሮና ቫይረስ የመዳን ሁኔታው ከፍተኛ በመሆኑ መፍራትና መደናገጥ ሳይሆን ላለመያዝ መጠንቀቅ አስፈላጊ ነው ተባለ

የኮሮና ቫይረስ የመተላለፍ ፍጥነቱና ታክሞ የመዳን ሁኔታው ከፍተኛ መሆኑን በቫይረስ የሚመጡ በሽታዎች ተመራማሪው ተናገሩ፡፡
 (አብመድ) የዓለም ከፍተኛ የጤና ወረርሽን የሆነው የኮሮና ቫይረስ የመተላለፍ ፍጥነቱ እና የመዳን ሁኔታው በጣም ከፍተኛ፤ ለሞት የመዳረግ ዕድሉ ደግሞ ዝቅተኛ በመሆኑ መፍራት እና መደናገጥ ሳይሆን ላለመያዝ መጠንቀቅ እንደሚያስፈልግ በአርማወር የምርምር ኢንስቲትዩት በቫይረስ የሚመጡ በሽታዎች ከፍተኛ ተመራማሪ አንዳርጋቸዉ ሙሉ (ዶክተር) ተናገሩ፡፡
ምልክቱ የታየባቸዉ ሰዎች ወደ ማቆያ ማዕከል እንዲሄዱ የሚመከረዉ ምን አልባትም ቫይረሱ ካለባቸዉ ቶሎ ታክመው እንዲያገግሙ እና የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት እንጅ ለሌላ እንዳልሆነም ኅብረተሰቡ ሊገነዘብ እንደሚገባ ዶክተር አንዳርጋቸው መክረዋል::
የኮሮና ቫይረስ ጉፋን ከሚያመጡ ቫይረሶች መካከል እና የመተንፈሻ አካላትን ከሚያጠቁ በሽታዎች ውስጥ አንዱ መሆኑን ያመለከቱት ተመራማሪው የሚያሳያቸው ምልክቶችም ከጉንፋን ጋር ታዛማችነት ያላቸው እንደሆኑ አስረድተዋል፡፡ በመሆኑም የሚያስነጥሰ፣ የሚያስለውና ትኩሳት የተየበት ሰው ሁሉ ኮሮና ይዞታል ብ
ሎ መደናገጥ እንደማይገባ ግን መጠንቀቅ እንደሚያስፈልግ መክረዋል፡፡ ስጋቶች ሲያጋጥሙ ራስን ማስመርመር እና ማረጋገጥ እንደሚገባም ዶክተር አንዳርጋቸው አሳስበዋል፡፡
ምንም እንኳ የኮሮና ቫይረስ የመተላለፍ ፍጥነቱ ከፍተኛ ቢሆንም ታክሞ የመዳን ሁኔታው ከፍተኛ እና ለሞት የሚያበቀውም ከሁለት እስከ ሦስት በመቶ በመሆኑ መፍራት እና መደናገጥ እንደማያስፈልግ፣ ላለመያዝ ግን መጠንቀቅ አስፈላጊ መሆኑን ኅብረተሰቡ እንዲገነዘብ ተመራማሪው ጠቁመዋል፡፡
ምልክቱ የታየባቸው ሰዎች ወደ ሕክምና ማቆያ ማዕከል እንዲወሰዱ የሚደረገው ምን አልባትም ቫይረሱ ካለባቸዉ ቶሎ ታክመዉ እንዲያገገግሙና ቫይረሱ ለቤተሰቦቻቸው እና ሌላዉ ማኅበረሰብ እንዳይዛመት በሚል ስለሆነ ተባባሪ መሆን እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡
‘‘ከሁሉም የሰውነት አካሎቻችን የበለጠ ከአፍጫችን፣ ዓይናችን እና አፋችን ጋር ቶሎ ቶሎ ግኝኙነት ያለው እጃችን በመሆኑና ምን አልባት ቫይረሱን በእጃችን ከነካነው በቀላሉ ደሰውነታችን ሊገባ ስለሚችል በውኃ እና ሳሙና በደንብ ቶሎ ቶሎ መታጣብ ፣ ምልክት ከታየብን ወደ ሕክምና በመሄድ እራሳችን እና ወገናችን ከኮሮና ቫይረስ ልጠብቅ ይገባል’’ ብለዋል ተመራማሪው ዶክተር አንዳርጋቸው ሙሉ በመልእክታቸው፡፡

 


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV