ኮሮና ቫይረስ ከያዛቸው ሰዎች አብዛኛዎች ድነዋል እንጂ አልሞቱም! ~ (ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ አእምሮ)

ኮሮና ገባ ብሎ ፍርሃት፣ ድንጋጤና ጭንቀት አያስፈልግም!
ኮሮና ቫይረስ ከያዛቸው ሰዎች አብዛኛዎች ድነዋል እንጂ አልሞቱም! ~ (ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ አእምሮ)

እንደዚህ አይነት አዳዲስ በሽታዎች በተከሰቱባቸው የታሪክ አጋጣሚዎች ከበሽታው እኩል ሊባል በሚችል ደረጃ ሰዎችን የጎዳው የስነ-ልቦና ዝግጁነት አለመኖር ነው። ለዚህም ማግለልና መድሎ ለኤች አይ ቪ መ ስፋፋት የተጫወተውን ሚና ማስታወስ በቂ ነው። እናም ህዝባዊ ፍርሃትና ጭንቀት የሚፈጥሩ መልዕክቶችን ችላ በማለት በእውቀትና በእርጋት ነገሮችን ማስተናገድ ይገባናል። በሽታውን በስፋት ያጠኑት የዉሃን ተመራማሪዎች ቀጣዮቹን ወሳኝ ነጥቦች አስቀምጠዋል፤

– ኮሮና ቫይረስ አፍንጫ የማያረጥብ እና ደረቅ (አክታ ኣልባ) ሳል የሚያስከትል ሲሆን ከፍተኛ ትኩሳትና ላብ፣ ቶሎ ቶሎ መተንፈስ ወይም ለመተንፈ ስ መቸገር ዋና ዋናዎቹ መለያዎቹ ናቸው።

– ቫይረሱ ከ26-27 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ያለውን ሙቀት መቋቋም የማይችል በመሆኑ ይሞታል፡፡ እንደ ሻይ፣ ሾርባ ፣ ትኩስ ውሃ …ወዘተ ያለትን ትኩስ ነገሮች በየቀኑ ደጋግሞ መጠጣትን ብዙሀኑ መክረዋል፡፡ (ትኩስ ነገሮችን መጠጣት ደግሞ ከባድ አይደለም፡፡)

– በጣም የቀዘቀዘ ውሃ አትጠጡ፣ የበረዶ ኩቦችን ወይም አመዳይ/Snow አትመገቡ! ( ባገራችን ልጆች ዘንድ የተለመደው ጀላቲም አይመከርም።)
– የምትችሉ ሁሉ የጸሐይ ሙቀት ተቀበሉ፡፡

– ኮሮና ቫይረስ ከ400-500 ናኖሜትር ዳያሜትር ርዝመት ያለው ትልቅ ቫይረስ በመሆኑ ለመከላከል የሚያስፈልገው ጭምብል ወይም ማስክ በተለየ መንገድ የተሰራ መሆን የለበትም፡፡ ማንኛውንም አይነት ጭምብል መጠቀም ይቻላል፡፡ (ማስኩ ግን በተለይ የሚያስፈልገው ምልክቱ ላላቸው ሰዎች ነው!)

– በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች በሚገኙባቸው ተቋማት የሚያክሙ የጤና ባለሙያዎች ግን የተለዩ የመከላከያ መንገዶችን መጠቀም አለባቸው፡፡

– በቫይረሱ የተጠቃ ሰው ከፊት ለፊታችሁ ከ3 ሜትር ርቀት ላይ ቢያስነጥስ ቫይረሶቹ ወደ ምድር የሚወድቁ በመሆናቸው በቫይረሱ ተጠቂ አትሆኑም።
– ቫይረሱ ብረትነት ባላቸው ገጾች/አካሎች ላይ ካረፈ በኋላ ለ12 ሠዓታት በህይወት ሊኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ ከብረት የተሰሩ እንደ እጀታዎች፣ በሮች፣ የቤት ዕቃዎችን፣ የአውቶቡስ የባቡር መደገፊያ እጀታዎችን ወይም ምሰሶዎችን ከነካችሁ በኋላ እጃችሁን በደምብ በሳሙና መታጠብ ይገባል፡፡

– ቫይረሱ በልብስ እና በጨርቆች ውስጥ ተሰግስጎ ከ6-12 ሰዓታት ሊኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ መታጠብ የሚችሉትን ልብሶች በሳሙናዎች ብናጥባቸው ቫይረሱን ይገድለዋል፡፡

-በየእለቱ መታጠብ የማይችሉ ልብሶችን ጸሐይ ላይ ብታሰጧቸው ቫይረሱን የጸሐይ ሙቀት ያዳክመዋል፡፡

በቫይረሱ ላለመያዝ ምን ማድረግ ይገባል?
1. የቫይረሱ ስርጭት በአብዛኛው ቀጥታ ከንክኪ ጋር የተያያዘ ሲሆን ቫይረሱ ያረፈባቸውን ቁሳቁሶች እና ልብሶች ወዘተ… መጠቀም ዋነኛ መተላለፊያው መንገዱ ነው፡፡ ይህም ማናቸውንም ነገር ከነኩ በኋላ በተደጋጋሚ እጅን በደምብ መታጠብ ዋነኛ መከላከያዎች ናቸው።

2. ቫይረሱ በሰው እጅ ላይ በሕይወት የሚቆየው 10 ደቂቃ ያህል ነው፡፡ ይሁን እንጂ በ10 ደቂቃዎች ውስጥ ብዙ ነገር ሊከናወን ይችላል፡- አይንን ማሸት፣ አፍንጫን መንካት፣ ጣቶችን ወደ አፍ መውሰድ [አፍንጫ ማሸትና ጥፍር የመመጥመጥ ክፉ ልማድ] ቫይረሱን በቀላሉ ወደ ጉሮሮ እንዲሄድ ያደርገዋል፡፡

3. ለራሳችሁና ለሌሎችም ደህንነት ስትሉ በጣም በተደጋጋሚ እጆቻችሁን ታጠቡ፡፡

4. ትኩስ ነገሮችን አብዝቶ መጠጣት አትርሱ!

ፈጣሪ አገራችንና ህዝቦቿን ከክፉ ይጠብቅልን!