ለቅዳሜ ሰኔ 16 ለዶ/ር አብይ ድጋፍ በመስቀል አደባባይ የተጠራው ሰልፍ አስተባባሪዎች መግለጫ ሰጡ

ሰኔ 16 በአዲስ አበባ የድጋፍ ሰልፍ ሊካሄድ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚ/ር ዓብይ አህመድ የወሰዷቸውን የማሻሻያ ሀሳቦች በመደገፍ ሰኔ 16 ሰልፍ ሊካሄድ ነው፡፡

በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የሚካሄደው ሰልፍ ጭብጥ ምክንያት አድርጎ የሚካሄድ ነው ሲል የሰልፉ አስተባበሪ ኮሚቴ ዛሬ በኢሌሌ ሆቴል ባደረገው ጋዜጣዊ መግለጫ አስረድቷል።

ሰልፉን ለማድረግም ከመንግስት ፍቃድ እንዲሰጣቸው በመጠባበቅ ላይ ናቸው፡፡ የሰልፉ አስተባበሪ አቶ ጉደታ ገላልቻ አበሰጡት መግለጫ ሰልፉ የፓርቲ አጀንዳን አያስተናግድም፡፡ በሰልፉ የአዲስ አበባና አካባቢው ነዋሪዎች ተሳታፊዎች ናቸው፡፡ ዓላማውም የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ምስጋና ለማቅረብ ነው፡፡