ብፁዕ አቡነ አረጋዊ: የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት እና የጅቡቲ አብያተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ኾነው ተመደቡ

የምልአተ ጉባኤ አስቸኳይ ስብሰባውን እያካሔደ የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ብፁዕ አቡነ አረጋዊን፣ የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት እና የጅቡቲ አብያተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ እንዲኾኑ መደባቸው፡፡ ብፁዕነታቸው የተመደቡት፣ ባለፈው ታኅሣሥ መጨረሻ ባረፉት ብፁዕ አቡነ ዳንኤል ምትክ ነው፡፡ በመኾኑም፣ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ፣ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የውጭ ግንኙነት መምሪያ እና የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት የበላይ ሓላፊነታቸውን እንደያዙ፣ የድሬዳዋ …