በቦሌ ክ/ከተማ በኦርቶዶክሳውያን ላይ በተፈጸመው የግፍ ግድያ እና በቀጠለው የጸጥታ ኀይሎች ማሸማቀቅ ቅ/ሲኖዶስ መንግሥትን ተቸ፤ ም/ል ከንቲባውን ነገ ያነጋግራል

ለዛሬ ሰኞ የካቲት 9 ቀን 2012 ዓ.ም. የምልአተ ጉባኤ አስቸኳይ ስብሰባ የጠራው ቅዱስ ሲኖዶስ፣ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4/ቀበሌ 24/፣ በኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች ላይ በተፈጸመው የግፍ ግድያ እና በቀጠለው የጸጥታ ኀይሎች ማሸማቀቅ፣ የመንግሥትን ርምጃ ተችቷል፡፡ ገዳዮች ለፍርድ እንዲቀርቡ የጠየቀ ሲኾን፣ ምክትል ከንቲባ ታከለ ዑማን፣ ነገ ከቀትር በኋላ ያነጋግራል፤ መሥዋዕት በተከፈለበት እና አካል በጎደለበት ቦታ ቤተ ክርስቲያን …